በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን የጨንቻ ከተማ አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት የተለያዩ እቃዎችን ለሴክተር መ/ቤቶች አላቂ የጽ/መሣሪያዎችን፣ የጽዳት እቃዎችንና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን የጨንቻ ከተማ አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት የተለያዩ እቃዎችን ለሴክተር መ/ቤቶች አላቂ የጽ/መሣሪያዎችን፣ የጽዳት እቃዎችንና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Oct 01, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን የጨንቻ ከተማ አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት የተለያዩ እቃዎችን ለሴክተር መ/ቤቶች አላቂ የጽ/መሣሪያዎችን የጽዳት እቃዎችንና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ነጋዴዎች መወዳደር ይችላሉ፡፡

1/ በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈላችሁ፡፡

2/ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው/ያላት)፤

3/ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN NO) ያለው(ያላት)፤

4/ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያለዉ(ያላት) ፣

5/ የዕቃ አቅራቢነት ምስክር ወረቀት ያለው(ያላት)፣

6/ ቫት በዋጋ ማቅረቢያ ላይ ካልተገለጸ እንደተገለጸ ተደርጎ ይወሰዳል፤

7/ አሸናፊ ድርጅቱ ያሸነፋቸውን ዕቃዎች በራሱ ትራንስፖርትና ወጪ ወደ ጨንቻ ከተማ አስ/ር ፋ/ጽ/ቤት ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

8/ ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶችን ይህ ማስታወቅያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 በተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ከጨንቻ ከተማ አስ/ር ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 ቀርበው የማይመልስ 200 (ሁለት መቶ ብር) እያንዳንዱ ሰነድ በመክፍል መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡

5/ ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ/ ብር 20,000(ሃያ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋዝ CPO) ከዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር በማያያዝ ይዞ መቅረብ ይጠበቅበታል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ አንቀበልም፡፡

10/ የጨረታ ማስከብሪያ ዋስትና ፀንቶ የሚቆየው በጨረታ ያሸነፉትን ዕቃ ሙሉ በሙሉ እስኪያቀርቡ ድረስ ነው

11/ ጨረታው የሚከፈተው በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 5፡30 የጨረታ ሳጥን ታሽጎ በዕለቱ በ8፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡

12/ በጨረታ ሰነድ ላይ የተገለጸው ዋጋ ከውል ጊዜ ጀምሮ ለ60 ቀናት የፀና ይሆናል፡፡

13/ ተጫራቾች ሁሉንም ሰነዶቻቸውን ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ በማድረግ በታሸገ ፖስታ የጨረታ ዋጋ ማቅርቢያ ሰነድ ዝርዝር ሙሉ በሙሉ በመሙላት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

14/ አሸናፊ ድርጅቱ ውል ሲገባ ውል ማስከበሪያ 10% (CPO) ማስያዝ አለበት አለበለዚያ በውሉ መሰረት ቅድመ ክፍያ ሳይቀበል ዕቃውን ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡

ማሳሰቢያ፦ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ ሞባይል ስልክ ቁጥር፡- 09 16 881 031 ይደውሉ:: በደቡብ ኢትዮጲያ ክልል በጋሞ ዞን የጨንቻ ከተማ አስ/ር ፋ/ጽ/ቤት ከአርባ ምንጭ 37 ኪ.ሜ ርቅት ላይ ትገኛለች።

በደ/ኢ/ክ/መ/ በጋሞ ዞን የጨንቻ ከተማ አስ/ር ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *