የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት የተለያዩ እቃዎች ግዢ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት የተለያዩ እቃዎች ግዢ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


2merkato.com (Oct 01, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 4/2019

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ እቃዎች ግዢ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፤

  1. የተለያዩ ተሽከርካሪዎች፡- በኤሌትሪክ የሚሰራ እስከ 30 ሰው የመጫን አቅም ያለው ተሽከርካሪ፣ 1/አንድ/ ቶን ክብደት የመጫን አቅም ያለው የኤሌክትሪክ ሻንሲ ካቢን ግዥ፣ 3/ሦሥት/ ቶን ክብደት የመጫን አቅም ያለው የኤሌትሪክ ሻንሲ ካቢን ግዥ፣ 3/ሦሥት/ ቶን የመሸከም አቅም ያለው የቆሻሻ ማጓጓዣ መኪና፣ በኤሌክትሪክ የሚሰራ አውቶሞቢል፣ በኤሌትሪክ የሚሰራ ፎርክሊፍት፣ የኤሌትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጀር፣ በሻንሲ ላይ የሚጫን ቦቲ ግዥ
  2. የተለያዩ መሳሪያዎች ግዥ፡- የበሬ ክብደት ማንሻ ማሽን፣ የፍርንባ መቁረጫ ማሽን፣ የጐድን መሰንጠቂያ ማሽን፣ ሸሆና ጥፍር መንቀያ ማሽን፣ ሰርቦ ሞተር፣ Electrical Motor with Gear BoX ግዥ
  3. የተለያዩ ፓምፖች ግዥ፡- የሞራ መሳቢያ ፓምኘ፣ ሰብመርሰብል ፓምኘ፣ Submerseble trash pump፣ ላሚል ፓምኘ ግዥ
  4. የብር መቁጠሪያ ማሽን፣ የውሃ ማጣሪያ፣ የተለያየ መጠን ያላቸው ፍሪጆች፣ አውቶክሌቭ ማሽን/ለክሊኒክ/፣
  5. የተለያየ መጠን ያላቸው ዲጂታል ሚዛኖች፣ የመበየጃ እና መቁረጫ ማሽኖች፣ የማዳበሪያ መስፊያ ማሽን፣ የማሸጊያ ማሽኖች
  6. የተለያዩ ኬሚካሎች፣
  7. የተሽከርካሪ በልቦች፣ ባትሪዎች እና ጎማዎች፣
  8. ለህንፃ እና ለቢሮ ዕቃዎች ጥገና የሚያገለግሉ ዕቃዎች ግዥ፣

ማንኛውም ተጫራች፡-

  • በዘርፉ ወይም በተመሳሳይ ህጋዊና የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያለው፣ ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን እና የታክስ ክፍያ መለያ ቁጥር(TIN) የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ፣ተጫራቾች ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ ስለመሆናቸው በግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን የተሰጠ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የታደሰ ክሊራንስ እንዲሁም በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
  • ከተራ ቁጥር 1-3 ለተጠቀሱት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 1000/አንድ ሺህ ብር/ እንዲሁም ከተራ ቁጥር 4-8 ለተጠቀሱት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 500/አምስት መቶ ብር/ በመክፈል በስራ ሰዓት ከግዥና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 3ዐ ዝርዝር መረጃ የያዘውን የጨረታ ሠነድ ማግኘት ይችላል፣
  • የጨረታ ማስከበሪያ /ቢድቦንድ/ ለሚጫረትበት የጠቅላላ ዋጋውን 2% በሲ.ፒ.ኦ፣ በባንክ ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ በድርጅቱ ደረሰኝ ማስያዝ ይኖርበታል፣
  • የጨረታ ሰነዶችና ከጨረታው ጋር ተያያዥ የሆኑ ሠነዶችን በፖስታ በማሸግ ከጨረታ መዝጊያው ሰዓት በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት፣
  • ጨረታው ጥቅምት 12 ቀን 2019 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡ዐዐ ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡3ዐ ሰዓት ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ውስጥ ይከፈታል፡፡ በጨረታ አከፋፈት ሂደት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙ የጨረታ ሂደቱን አያስተጓጉለውም፡፡
  • ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር ዐ11466-47-05 መጠየቅ ይቻላል፡፡

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት