በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የከለላ ከተማ አስተዳደር ገን/ጽ/ቤት የመኪና መለዋወጫ እቃ/እስፔር ፓርት/ እና የመኪና ጎማ ከነ ካለማደሪያ በግልጽ ጨረታ አወዳደሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የከለላ ከተማ አስተዳደር ገን/ጽ/ቤት የመኪና መለዋወጫ እቃ/እስፔር ፓርት/ እና የመኪና ጎማ ከነ ካለማደሪያ በግልጽ ጨረታ አወዳደሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Oct 02, 2026)

ብሄራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የከለላ ከተማ አስተዳደር ገን/ጽ/ቤት የግዥ እና ንብረት ቡድን የስራ ከፍል ለከለላ ከተማ አስተዳደር ሴ/መ/ቤቶች ለ2019 በጀት ዓመት ከያዙት በጀት ላይ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ መሰረት፡-

  • ሎት 1 ፡- የመኪና መለዋወጫ እቃ/ እስፔር ፓርት/
  • ሎት 2 ፡- የመኪና ጎማ ከነ ካለማደሪያ በግልጽ ጨረታ አወዳደሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ ጨረታውን መወዳደር ለምትፈልጉ ትክክለኛ ዋጋዎን እንድትሞሉ እና እንድትወዳደሩ ያስታውቃል። በመሆኑም በዘርፉ የተሰማሩ ለጨረታው ብቁ የሆናችሁ ድርጀት የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባችኃል።

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው።
  2. የግዥ መጠን ብር ከ500,000 (አምስት መቶ ሺህ)ብር እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  3. ተወዳዳሪዎች በግብር አመቱ ተገቢውን የታክስ እና ግብር ግዴታ የተወጡ መሆኑ የሚያሳያሳይ የታክስ ከሊራስ ማቅረብ የሚችል። ከ 1 እስከ 2 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻችሁ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 2% በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1(ደረሰኝ)፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው።
  5. የውድድሩ ሁኔታ በጠቅላላ ድምር በሎት መቀመጥ አለበት።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት ሲመጡ የማይመለስ 200 ብር በመያዝ በከለላ ከተማ አስተዳደር ገን/ጽ/ቤት የግዥ ቡድን የስራ ክፍል ድረስ በአካል በመምጣት መግዛት የምትችሉ መሆኑን ያሳውቃል።
  7. በጨረታው የተሳተፋችሁ ተጫራቾች ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከለላ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥ ቡድን የስራ ክፍል ቢሮ ቁጥር 02 ድረስ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 09 45 48 88 42/ 09 14 36 17 16 ላይ በመደወል ማብራሪያ ማግኘት ይቻላል። ዝርዝሩ ከዋጋ መሙያ ጋር ተያያዞ የሚሸጥ ይሆናል።
  8. ተጫራቾች በጨረታው አሸናፊነታቸው ከታወቀ በ5 ቀን ውስጥ የሞላውን ጠቅላላ ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10% በማስያዝ በከለላ ወረዳ ዓቃቤ ህግ ጽ/ቤት ውል መግባት አለባቸው።
  9. ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ከቀን 21/01/2019 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 30/01/2019 ዓ.ም ለተከታታይ ቀናት የሚቆይ ይሆናል። ሁሉም ተጫራቾች ከላይ ከተገለጸው ቀን ቆይታ በኋላ በቀን 1/02/2019 ዓ.ም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በከለላ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 04 ከጠዋቱ በ4፡00 ይከፈታል። ሆኖም ግን ተጫራቾች በራሳቸው ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ባይገኙም የጨረታውን መክፈት የማያስተጓጉል እና በተጨማሪ በጨረታ ሂደቱ ለሚተላለፍ ውሳኔዎች ተገዢ ይሆናሉ።
  10. የጨረታው መክፈቻ ጊዜ የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
  11. ጨረታውን ሆን ብሎ ለማዛባት የሚሞክር ተጫራች በመንግስት ግዥ ላይ እንዳይወዳደርየአ/ ብ/ክ/መ/የመንግስት ግዥ መመሪያ ቁጥር 144/2018 በአንቀጽ 154 ከጨረታው ውጭ እንደሚሆን መመሪያው በግልጽ ያስረዳ። ስለዚህ ያስያዘውም የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወረስ ይሆናል።
  12. የጨረታ የመዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
  13. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ስማቸውን፤ ፊርማቸውን፤ ሙሉ አድራሻቸውን ፤ ማስፈር እና የድርጁቱን ማህተም ማድረግ ይኖርባቸዋል።
  14. መ/ቤቱ የስራውን 20% የመጨመር ሆነ የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  15. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ድርጂት በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን የመኪና መለዋወጫ እቃ እና ጎማ ግዥ ጥራታቸውን የጠበቀ መሆን ይኖርባቸዋል።
  16. በጨረታ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝፓራፍ እንዳይኖር በጥንቃቄ መሞላት እንዳለበት እያሳሰብን ነገር ግን ስርዝ ድልዝ ካለው ውድቅ የሚደረግ መሆኑን እንገልጻለን።
  17. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

በደቡብ ወሎ ዞን የከለላ ከተማ አስተዳደር ገን/ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *