Addis Zemen (Oct 02, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የካ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ኮተቤ የመጀ ደ/ት/ቤት ለ2019ዓ.ም የሚከተሉትን ዕቃዎች በአንደኛ ዙር በግልፅ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል።
- ሎት1፦ የደንብ ልብስ
- ሎት2፡- አላቂ የቢሮ እቃዎች
- ሎት3፡- የፅዳት እቃዎች
- ሎት 4 ፡- የት/ት ዕቃዎች
- ሎት5፡-የጥገና ዕቃዎች
- ሎት6፡-ሞንታርቦ
- ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ፣ የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬት፣ የግብር ክሊራንስ፣ በመንግስት እቃና አገልግሎት ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የተሰጠ ፈቃድ ሰርትፍኬት ከጨረታ ሰነዱ ጋር አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች በኮተቤ የመጀ/ደ/ት/ቤት ግቢ ክ/ሂ/ግ/ንብ/ቡድን መሪ ቢሮ በመገኘት ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ለ10 የስራ ቀናት በመቅረብ የጨረታውን ሰነድ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመግዛት የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራች ለሎት1፣2፣3፣4 ናሙናዎችን ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡እንዲሁም የመጻሀፍት ግዥ በፎቶ የተደገፈ ሳምፕል እና ለሎት 5 የጥገና ዕቃዎች ሳምፕል ማቅረብ የሚጠበቅባችሁ ዕቃዎች ላይ ናሙና ማቅረብ ሲጠበቅባችሁ ሳምፕል ማቅረብ የማይችል ዕቃዎች ላይ በፎቶ የተደገፈ ናሙና ማቅረብ ሲጠበቅባቸው ለሎት6 በፎቶ የተደገፈ ምስል እንዲሁም ሙሉ ለሙሉ የተጠቀሰውን ዕቃ የተሟላ ማብራሪያ የሚገልፅ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- በጨረታው ለመወዳደር ለሚፈልጉ ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ሎት የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም የባንክ ዋስትና በፖስታ በማሸግ ለእቃ ግዥው ለሎት1፦- 34,000.00(ሰላሳ አራት ሺህ ብር ብቻ )፣ ለሎት2፦ 24,000.00(ሃያ አራት ሺህ ብር ብቻ ) ፣ለሎት3፡-24,000.00(ሃያ አራት ሺህ ብር ብቻ)፣ ለሎት4፡- 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር ብቻ)፣ ለሎት5፡- 5000.00(አምስት ሺህ ብር ብቻ) ለሎት6-10,000.00(አስር ሺህ ብር ብቻ) ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ከሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ የጨረታው አሸናፊ እንደታወቀ ያስያዙት የጨረታ ሰነድ ማስረከቢያ ሲፒኦ ይመለስላችኋል።
- ተጫራቾች ቴክኒካል ኦርጅናል እና ኮፒ ፋይናንሻል ኦርጅናል እና ኮፒ ሰነዳቸውን እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያውን በተለያየ ፖስታ በማድረግ ሁሉም የታሸጉ ፖስታዎች በአንድ ትልቅ ፖስታ አሽገው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ያቀርባሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊ ሆነው የተገኙባቸውን ዕቃዎች ከአጠቃላይ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ የማስያዝና የግዥ ውል ስምምነት መፈፀም ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በ11ኛው ቀን 4፡30 ታሽጎ በ11ኛው ቀን 5፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮተቤ የመጀ/ደ/ት/ቤት ግቢ ክ/ሂ/ግ/ንብ ቡድን መሪ ቢሮ ይከፈታል።
- ት/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡-ኮተቤ አዋሽ ባንክ ፊት ለፊት ባለው አስፋልት መንገድ ገባ ብሎ (መምህራን ኮሌጅ በስተጀርባ በኮተቤ የመጀ/ደ/ት/ቤት ግቢ ስ.ቁ 0118 68 40 22 ወይም 011868 4021
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የካ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ኮተቤ የመጀ/ደ/ ት / ቤት