Addis Zemen (Oct 02, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
ማስታወቂያ ቁጥር የኮ/ ዲ/ግ/ማ / ድ / ግ / ጨ / ቁ /03/2019
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት ፑሚስ ከነትራንስፖርቱ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም
1. በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችል በዘርፉ የተሰጠ የታደሠ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸዉ ማስረጃ ኮፒ አያይዘዉ ማቅረብ የሚችሉ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ) ብር በመክፈል በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ቢሮ አጠገብ የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት ቢሮ በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ መግዛት ይችላሉ።
2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ ከታወቀ ባንክ የሚሰጥ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (unconditional bid bond guarantee) ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
3. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተዘግቶ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 5፡00 ተሳታፊዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
4. የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ቢሮ አጠገብ
ስልክ ቁጥር 09-13-56-49-36/0911-15-60-36
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት