2merkato.com (Oct 02, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
ጣምራ ለማህበራዊ ልማት ድርጅት ከተመሠረተበት 1990 ዓ.ም ጊዜ ጀምሮ ላለፉት 29 ዓመታት በወጣቶች ልማት፣ በሥነ-ተዋልዶ ጤና፣ በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚደርሰውን ጾታዊ ጥቃት በመከላከል፣ በአካባቢ ጥበቃና የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ስርጭትና በሌሎች ማህበራዊ አገልግሎቶች ዙሪያ በኦሮሚያ፣ በደቡብ ክልሎችና በአዲስ አበባ መጠነ ሰፊ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡ ለዚህም ተግባሩ ድርጅታችን ላበረከተው የማኅበረሰብ አቀፍ ጉልህ አስተዋኦ ከሻሸመኔ ከተማ አስተዳደር፣ ከኦሮምያ ክልልና ከኢፊዲሪ መንግስት የሠርትፍኬት፣ የዋንጫ፣ የቦታና የመኪና ሽልማቶችን ያገኘ አንጋፋ ድርጅት ነው፡፡
ድርጅታችን ጣምራ ለማህበራዊ ልማት ድርጅት በሲዳማ እና በኦሮሚያ ክልል እየተገበረ ለሚገኘው ICD ፕሮጀክት የሚውል የድንች (ጉደኔ) የዘር አይነት በኩንታል መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም የዚህን ጨረታ ዝርዝር የያዘውን ዶክመንት የማይመለስ 200 ብር በመክፈል፤ የጨረታ ሰነድ መግዛት እና ጨረታውን መሳተፍ የምትችሉ ሲሆን ተጫራች ድርጅቶች ተወካይ መላክ የምትችሉ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡
አድራሻ – ከጃክሮስ ወደ ሳህሊተ ምህረት ቤተክርቲያን በሚወስደው መንገድ አቢሲኒያ ባንክ ጀርባ እንገኛለን
ለበለጠ መረጃ – +251 982024874 / +251 970793680 ይደውሉ፡፡
Deadline – አርብ ፣ መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም (Monday, October 5, 2026 , by 11:00 PM)