Addis Zemen (Oct 03, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
ማስታወቂያ ቁጥር 01/2019
በኢትዮጵያ የግበርና ምርምር ኢንስቲትዩት በብሔራዊ የግብርና ባዮቴክኖሎጂ ምርምር ማዕከል በ2019 በጀት ዓመት ለምርምር ስራ የሚውሉ የኬሚካል እና የምርምር ግብዓቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚህ የሥራ መስክ የተሰማራችሁና በጨረታው ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች
1.ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድና ማረጋገጫ ፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) እና ሰርተፍኬት ፤ ቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ በግዥ ኤጀንሲ በአቅራቢነት የተመዘገቡና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
2. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 /አስር/ የስራ ቀናት ውስጥ በሆለታ ብሔራዊ የግብርና ባዮቴክኖሎጂ ምርምር ማዕከል ቢሮ ቁጥር 41 /ግዥ ክፍል/ በመቅረብ የማይመለስ ብር 600.00 /ስድስት መቶ/ በመከፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚቻል ሲሆን ሰነዱን መ/ቤቱ ባቀረበው ስፔስፍኬሽን መሰረት በትክክል በመሞላት በድርጅቱ ባለቤት ወይም ህጋዊ ወኪል ተፈርሞ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የጨረታው ማስታወቅያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 /በአስረኛው/የስራ ቀን እስከ ጠዋት 4፡00 /አራት ሰዓት/ ማስገባት ይቻላል።
3. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በተለያዩ ፖስታዎች በማሸግ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት መለየት አለባቸው
4. የጨረታ ማስከበርያ ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ/ በባንክ በተመሰከረለት ሲ.ፒ.ኦ/ CPO/ ብቻ ማስያዝ አለባቸው፤
5. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ከፍት ይሆናል።
6. የጨረታው ሳጥን የጨረታው ማስታወቅያ በጋዜጣ ከወጣበት በ10ኛው የስራ ቀን ላይ ከጠዋት 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ /ታሽጎ/ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማዕከሉ አዳራሽ ይከፈታል።
7. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈባቸውን ዕቃዎችን ሙሉ በሙሉ ማዕከሉ ድረስ ማቅረብ አለበት።
8. ማዕከሉ ለግዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ -ሇለታ
የቢሮ ስልክ ቁጥር-011 261 0611
በኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት በብሔራዊ የግብርና ባዮቴክኖሎጂ ምርምር ማዕከል