Addis Zemen (Oct 03, 2026)
የግዢ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨስቁ.:-NCB-AAMMI-002/2019
በኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ አዳማ የግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ለ2019 በጀት ዓመት የምርት ሥራ አጋዥ የሆኑ ለኦፕሬሽናል ሥራዎች አጋዥ የሆኑ የወርክ ሾፕ ማሽኖች በዚህ የጨረታ ሰነድ በተገለፀው መሰረት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ሎት-1፡- ለኦፕሬሽናል ሥራዎች አጋዥ የሆኑ የወርክ ሾፕ ማሽኖች
- በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ያህል ሰነዱን አዳማ የግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ በግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 014 በመገኘት መውሰድ (መግዛት) ይችላሉ።
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት እቃ ጋር ተዛማጅ የሆነ በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክረ ወረቀት፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የቫት ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም የግብር ክሊራንስ ጨረታ ለመሳተፍ የሚስጥ/ የሚያስችል ምዝገባ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተወዳዳሪዎች በጨረታው ላቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ በጨረታ መመሪያው ላይ የተገለጸውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው። የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በተጫራቹ ምርጫ ከሚከተሉት ዓይነቶች አንዱ ሊሆን ይችላል።
(ሀ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና፣
(ለ) በጥሬ ገንዘብ ወይም በታወቀ ባንክ የተረጋገጠ ቼክ ወይም የክፍያ ትዕዛዝ/CPO/ የባንክ ጋራንቲው 60 ቀንና ከዚያ በላይ መሆን አለበት፣
ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት (አስር የሥራ ቀናት) በአዳማ የግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ በግዢ ክፍል ቢሮ ቁጥር 014 በመገኘት ሰነዱን በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተገለፀው አስተሻሸግ መሰረት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
ጨረታው የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስር የስራ ቀናትን አልፎ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከታች በተገለፀው አድራሻ በአዳማ የግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ የስብሰባ አዳራሽ ጨረታው ይከፈታል። ቀኑ የበዓል ወይም የእረፍት ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት ይከፈታል። የተጫራች አለመኖር ፖስታው ተሟልቶ እስከተገኘ ድረስ ጨረታውን ከመክፈት አያስተጓጉልም።
ኢንዱስትሪው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 022 111 0689 / 09 12 26 46 80 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።
አድራሻ፡- አዳማ ከወንጂ ማዞሪያ ተቃራኒ አቅጣጫ 500ሜ ላይ ስልክ፡- 09 12 26 46 80/ 09 20 86 53 44
ፋክስ፡-022 111 1866
አዳማ
በኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ አዳማ የግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ