Addis Zemen (Oct 04, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፦ ECMA/NCB/OB/02/2019
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ባለው በጀት የቢሮ ቦታ ኪራይ ግዥ (Procurement of Rental of Secure Office Space) ግዥ በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አገልግሎቱን ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት፦
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን እና ሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መክፈቻ ቀን ድረስ የማይመለስ 300.00 (ሶስት መቶ ብር/በመ/ቤታችን አካውንት 1000586364824 ገቢ በማድረግ ከባለሥልጣኑ ፋይናንስና ግዥ ክፍል የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የመወዳደርያ ሰነዳቸውን ፋይናንስና ቴክኒካል ኦሪጅናልና ኮፒ ለየብቻ በማሸግ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ጨረታው መዝጊያ ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በዘርፉ ያላቸውን በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የግብር ክሊራንስ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፤ በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድረ-ገጽ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ማስረጃቸውን እንዲሁም የተፈረመና ማህተም ያለው የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈፀም ቃል የተገባበት ቅጽ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች ዋጋቸውን በመሙላት ባለሥልጣኑ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከጨረታ መዝጊያ ሰዓት በፊት ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርቡና ስርዝ ድልዝ ያለው የጨረታ መወዳደሪያ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
- ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ለ15 ቀናት ብቻ ነው።
- ተጫራቾች በሚያቀርቧቸው ሰነዶች ላይ የድርጅታቸውን ማህተምና የተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪል ፊርማ መኖር ይገባዋል።
- አሸናፊው ተጫራች አገልግሎቱ በተፈለገ ጊዜ አገልግሎቱን የመስጠት ሃላፊነት አለበት።
- ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበርያነት የብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ዋስትና ወይም ሲፒኦ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የቀረበውን ዝርዝር መስፈርት መሰረት በማድረግ የሚያቀርቡትን አገልግሎት ዝርዝር የቴክኒክ መግለጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
- አንዱ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
- ጨረታው ጥቅምት 9 ቀን 2019 ከሰዓት በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከሰዓት በ4፡30 ላይ ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በባለስልጣኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
- በጨረታው መክፈቻ ዕለት የተጫራቾች አለመኖር የጨረታውን ከፈት አያስተጓጉለውም።
- ባለሥልጣኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጨማሪ ማብራርያ ካስፈለገ በአካል የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን አድራሻ ቦሌ መንገድ ፍላሚንጎ ሬስቶራንት ገባ ብሎ ባለው ዋ/መ/ቤት በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ።
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን
የፋይናንስና ግዥ ዳይሬክቶሬት
ከፍላሚንጎ ሪስቶራንት ወደ አደራ ሆስፒታል በሚወስደው መንገድ ምናዬ ህንፃ
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
ስልክ 011-5-57-83-27
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን