የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የግራውንድ ሰርቪስ ሠራተኞች ዩኒፎርም አምራች ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በኮንትራት ለማሠራት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የግራውንድ ሰርቪስ ሠራተኞች ዩኒፎርም አምራች ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በኮንትራት ለማሠራት ይፈልጋል


Addis Zemen (Oct 05, 2026)

የግራውንድ ሰርቪስ ሠራተኞች ዩኒፎርም ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር SSNT-T646

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የግራውንድ ሰርቪስ ሠራተኞች ዩኒፎርም አምራች ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በኮንትራት ለማሠራት ይፈልጋል።

በመሆኑም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አምራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡–

1. ለሥራው ብቁ የሆኑ ተጫራቾች እና በሙያ ዘርፉ ሰባት ዓመት እና ከዚያ በላይ የሠሩ፣ የዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግሥት ጨረታዎች ለመሳተፍ ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።

2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የሥራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ 200.00 ብር ሁለት መቶ ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T646 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ቅጅ (Deposit Slip Copy) ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ።

3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ መቶ ሺህ ብር (100,000) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ለ120 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከማንኛውም ኢንሹራንስ የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ተጫራቾችን የጨረታ ማስከበሪያ ለተጨማሪ ቀን የሚቆይበት ጊዜ እንዲራዘምለት የመጠየቅ መብት አለው።

4. ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን (ቴክኒካል እና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ቅጂውን እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ በተለያየ ኤንቨሎፕ አሽገው ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል ማክሰኞ ጥቅምት 24 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ 8:00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተመሳሳይ ቀን 8፡30 በቦሌ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መሥሪያ ቤት በጨረታ መክፈቻ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል።

ለተጨማሪ ማብራሪያ፦

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ

ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ

ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል

ቅድስት ታሪኩ

በስልክ ቁጥር፡ +251-11 517-8025 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።

ኢሜል: KidistTa@ethiopianairlines.com

አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *