የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ ፍራሽ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ ፍራሽ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Oct 10, 2026)

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ኢት/ያ ክልል የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ ለ2019 በጀት ዓመት በጨረታ ቁጥር ሶከፋ/01/2019 ዓ/ም ፍራሽ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

1. የጨረታ ቁጥር ሶከፋ/01/2019 ዓ/ም ፍራሽ ግዥ ጨረታዉን ለመሳተፍ የሚፈልጉት፡- 

2. በጨረታዉ መሳተፍ የሚፈልጉት በሚመለከታቸዉ መስሪያ ቤቶች በአቅራቢነት የተመዘገቡና ለ2019 በጀት ዓመት በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፣ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና በ EGP የተመዘገቡ፣ ከዚህ በፊት ላከናወናቸዉ ተመሳሳይ ሥራዎች አገልግሎቶች ከአሠሪዉ አካል የመልካም ሥራ አፈጸጻም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መወዳደር ይችላሉ።

3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት (አስራ አምስት ቀናት) ከታች ከተጠቀሰዉ አድራሻ መግዛት ይችላሉ።

4. የተዘጋጀዉን መደበኛ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 500.00 (አምስት መቶ ብር) በማቅረብ መግዛት ይችላሉ። የጨረታ ሰነድ የሚገኝበት ቦታ ወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ ግዥ ንብረት አስተዳደር ዋና ሥራ ሂደት ቢሮ ይገኛል።

5. ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ 16ኛዉ ቀን ከቀኑ 4፡00 (አራት ሰዓት) ድረስ ለጨረታዉ በተዘጋጀዉ ሳጥን ውስጥ የጨረታ ሰነድ ማስገባት ይችላሉ። ዘገይቶ የሚቀርብ ጨረታ ተቀባይነት አይኖረውም ሳይከፈት ለተጫራቹ ይመለስለታል።

6. ጨረታው የሚከፈተው ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውና ሌሎች መገኘት የሚፈልጉ ባሉበት በ16ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ላይ ታሽጎ በዕለቱ ከቀኑ 4፡30 የሚከፈት ይሆናል። 16ኛው ቀን የበአላት ቀን ከሆነ (የሥራ ቀን ካልሆነ) በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።

7. ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

8. ርክክብ የሚፈጸምበት ቦታ ወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳዳር ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ ቅጥር ግቢ ዉስጥ ይሆናል።

9. የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ 0461800863 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኘላን ልማት መምሪያ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *