Be'kur (Oct 12, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የታች አርማጭሆ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት አመት ለወረዳው ሴክትር መሥሪ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ
- ሎት 1. የ1 HZ ተሽከርካሪ መለዋወጫ፣
- ሎት 2. የKUN-25 ተሽከርካሪ መለዋወጫ፣
- ሎት 3. የሪቮ ተሸከርካሪ፣
- ሎት 4. የጽህፈት መሳሪያ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አቅራቢዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ የሚመለከተው የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸው፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ታች አርማጭሆ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 7 በመምጣት የተሟላ የጨረታውን ዝርዝር ማስታወቂያና ሙሉ ጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡ ጨረታው ጋዜጣው ከወጣበት በ11ኛው ቀን በጨረታው ማስታወቂያ በተጠቀሰው ቦታ ቀንና ሰዓት ይከፈታል፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 273 01 34 /058 273 04 20 መደወል መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የታች አርማጭሆ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት