በምስራቅ ጎጃም መስ/ዞን የደ/ኤልያስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለተለያዩ አገልግሎት ሊውሉ የሚችሉ የጽህፈት መሳሪያ በዘርፉ ከተሰማሩ ነጋዴዎች መካከል አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በምስራቅ ጎጃም መስ/ዞን የደ/ኤልያስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለተለያዩ አገልግሎት ሊውሉ የሚችሉ የጽህፈት መሳሪያ በዘርፉ ከተሰማሩ ነጋዴዎች መካከል አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Be'kur (Oct 12, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በምስራቅ ጎጃም መስ/ዞን የደ/ኤልያስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥ/ን/አስ/ቡድን በወረዳችን ስር ለሚገኙ ሴ/መ/ቤቶች ከ2019 የመደበኛ በጀት ለተለያዩ አገልግሎት ሊውሉ የሚችሉ የጽህፈት መሳሪያ በዘርፉ ከተሰማሩ ነጋዴዎች መካከል አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት ያላቸው፡፡
  3. የታክስ ክሊራንስ ፣የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና ጨረታው ከብር 500,000 (አምስት መቶ ሽህ) ብር እና በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ የሚያቀርቡ ተጫራቾች መሳተፍ ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት ከደኤ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ድረስ በመቅረብ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ) በመክፈል የተዘጋጀውን የዕቃ ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ይዘጋና በዕለቱ የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጽ/ቤቱ የግዥ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 8 በግልጽ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በእለቱ በቦታው በራሳቸው ፈቃድ ባይገኙ የጨረታ አከፋፈት ስርዓቱን አያስተጓጉለውም፡፡
  5. በተጫራቾች የሚሞላው የጨረታ ሰነድ ለ45 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል፡፡
  6. ተጫራቾች በሞሉት የጨረታ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ 20,000 (ሀያ ሽህ) ብር በመ/ቤታችን መ/ሂ1 ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ፣ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ነገር ግን በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አይቻልም፡፡
  7. በተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ የጨረታ ዋጋ ፀንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ለ 28 ቀናት ወይም በድምሩ ለ 73 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን አለበት፡፡
  8. ተጫራቾች ዋጋ የሞሉበትን የጨረታ ሰነድ እና የጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ በታሸገ ፖስታ በአድራሻ ለደ/ኤ/ወ/ ገንዘብ ጽ/ቤት በማድረግ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም እና አድራሻ በመሙላት የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት፣የታክስ ክሊራስ ፣የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የቫት ተመዝጋቢነት የምስክር ወረቀት በማየያዝ እስከ 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም ተጫራቾች ዋጋ ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም ጨረታዉ የሚከፈትበት 11ኛው ቀን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት ጨረታው ይከፈታል፡፡
  9. አሸናፊው ድርጅት የአሸናፊነት ውጤት ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ውል መያዝ አለበት ፡፡ ውል ሲይዝ የውል ማስከበሪያ ያሸነፈበትን ዋጋ 10በመቶ በመ/ቤቱ መሂ/1 ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በሚያስቀምጠው አይነት ወይም ስ ፔስፊኬሽን መሰረት ሰነዳቸውን ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  11. አሸናፊው ድርጅት ወይም ግለሰብ የአሸነፈውን እቃ የደ/ኤልያስ ወረደ ሴ/መ/ቤቶች ንብረት ክፍል ድረስ በራሱ ወጭ በማጓጓዝ ማስረከብ ይኖርበታል፡፡
  12. በጨረታው ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ህጋዊ ተጫራቾች የበለጠ መረጃ ለማግኘት ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0582500485 ማግኘት ይቻላል፡፡
  13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. ውድድሩ በጥቅል ወይም በዋጋ ድምር በሎት መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  15. ሌሎች ያልተጠቀሱ አሰራሮች በአብክመ ግዥ መመሪያ ቁጥር 144/2018 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡

የደ/ኤልያስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *