በካርታው መሰረት ቤቱ ያረፈበት ስፋት 64.68ካ/ሜ ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ – test3.diretenders.com

በካርታው መሰረት ቤቱ ያረፈበት ስፋት 64.68ካ/ሜ ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ


Addis Zemen (Oct 12, 2026)

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት እየሩሳሌም አፈወርቅ እና የፍ/ባለዕዳ እነ አልማዝ ገብሬ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 19610 22/8/2018ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/123255ዓ.ም በ20/9/2018ዓ/ም በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 09 የቤት ቁጥር 338 የሆነ ቤት በካርታው መሰረት ቤቱ ያረፈበት ስፋት 64.68ካ/ሜ ከግቢው ለቤቱ የሚደርሰው ስፋት 12.73ካ/ሜ ካ/ሜ ጠቅላላ በፕሮፖርሽን የሚደርሰው የቦታ ስፋት 77.4 ካ/ሜ በልኬት የተገኘው ቤቱ ያረፈበት ስፋት 109.88ካ/ሜ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 4,874,282.98 (አራት ሚሊዮን ስምንት መቶ ሰባ አራት ሺህ ሁለት መቶ ሰማያ ሁለት ከ98/100) ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 4 ቀን 2019ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡  የተጫራቾች ምዝገባ 4፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የሐራጅ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡

ከ1/4ው አስበልጦምሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ5 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ከያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተዳርጎ ጨረታው ከበፊቱ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +25111 273 0852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የፌደራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃጸም ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *