የሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን በተለያዩ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ ለቱቦ ሥራ የሚሆን ሞልድ መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን በተለያዩ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ ለቱቦ ሥራ የሚሆን ሞልድ መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Oct 12, 2026)

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የግዢ መለያ ቁጥር፦ ሲ/መ/ባ/003/2019

የሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን በተለያዩ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ ለቱቦ ሥራ የሚሆን ሞልድ ከዚህ በታች በተገለጸው መሠረት መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ተ.ቁ

የዕቃው አይነት

ብዛት

1

ሞልድ Ø80 ሴ.ሜትር

8

2

ሞልድ Ø90CM ሴ.ሜትር

8

3

ሞልድ Ø1 ሜትር

8

4

ሞልድ Ø1.2M ሜትር

8

በዚሁ መሠረት፡-

1. የኮንስትራክሽን መሣሪያዎች አቅራቢነት ፍቃድ ያላቸው

2. ተጫራቾች አግባብነት ያለው ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሠርተፊኬት፣ የግብር ከፋይ ሰርተፊኬት እና በጨረታ መወዳደር የሚያስችል የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ታክስ ክሊራንስ እንዲሁም ከመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸውን የሚያሳይ ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. ከሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን ጋር ውለታ ገብቶ በአፈጻጸም ችግር ምክንያት ማስጠንቅቂያ የተሰጠ ሰነዱን መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችልም።

4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አሰስር) ተከታታይ ቀናት ከባለሥልጣኑ መ/ቤት ግዥ የፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮቁ ጥር 5 ቀርበው መግዛት ይችላሉ።

5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ(CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ የቀረበ የጨረታ ማስከበሪያ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና (unconditional Bid Bond) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል በተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 0.5% ማስያዝ ያለባቸው ሲሆን ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ከላይ በተገለጸው መሠረት ይሆናል። ከባንክ የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ለ120 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል።

6. የጨረታ ሰነዱ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ ጨረታ ማሰከበርያ /Bid Security/፣ ፋይናሻል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒዎችን እንዲሁም ቴክኒካል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒ ሰነዶች በተለያየ ፖስታ በሰም በማሸግ ለየብቻቸዉ ታሽጎ በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ ተካተውና በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመጻፍ ሕጋዊ የሆነ ማሕተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት በሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን በግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይረክቶሬት ክፍል ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ማስከበሪያው ከቴክኒካል ሠነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት። ሆኖም የተጠቀሰው ቀን የእረፍት ወይም የሕዝብ በዓል ቀን ሆኖ ከዋለ በቀጣይ በሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ላይ የሚከፈት ይሆናል።

7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወክሎቻቸው በተገኙበት ከላይ የጨረታ መክፈቻ ተብሎ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ በባለሥልጣኑ መ/ቤት አዳራሽ ይከፈታል።

ማሳሰቢያ፡- ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስልክ ቁጥር፡- 0462-128-446

ሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን

ሀዋሳ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *