Addis Zemen (Oct 14, 2026)
የዕቃ ግዥ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር 01/2019
የጨፌ ከረቡ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት በወረዳው ለሚገኙ የመንግስት መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ፡
- የጽህፈት መሳሪያዎችን፣
- የጽዳት እቃዎችን፣
- ቋሚ የቢሮ እቃዎችንና ኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የመወዳደሪያ መስፈርት
- በንግድ (በስራ) ዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የስራ ፍቃድ ያላቸውና በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ውስጥ የዘመኑን ግብር የከፈሉ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tin Number) ያላቸው እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ ከሆኑ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- እቃ አቅራቢዎች በእቃ አቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና ለመመዝገባቸው የታደሰ ሕጋዊ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረለት CPO ብቻ ብር 20,000/ ሃያ ሺህ/ ማስያዝ የሚችል፣
- እቃ አቅራቢው የሚገዛውን እቃ በራሱ የማጓጓዣ ወጪ መስሪያ ቤቱ ድረስ ማቅረብ የሚችል::
- የሚቀርበው ቋሚ የቢሮ ዕቃ ያልተገጣጠሙ ከሆኑ በራሱ ወጪ ማስገጠም የሚችል::
- የሚወዳደሩባቸውን የዕቃ አይነት ማለትም አላቂ የጽህፈት መሳሪያ፤አላቂ የጽዳት እቃዎችና ሳምፕል ወይም ናሙና ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
ማሳሰቢያ፡–
- ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርባቸው የምስክር ወረቀቶች በጉልህ የሚታዩና የሚነበቡ መሆን አለባቸው። የቀረበው ማስረጃ ግልጽነት የሌለውና የማይነበብ ከሆነ ዋጋ አይኖረውም።
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት በመወዳደሪያ ሃሳብ ሰነድና የጨረታውን መመሪያ ስለመቀበላቸው የሚያረጋግጥ በጨረታ ሰነዱና የጨረታ መመሪያ ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል ጽፈው ስልጣን ባለው አካል በመፈረም የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ዋናውንና ኮፒውን ለየብቻው በመለየት በፖስታ (Envelope) በማድረግና በሰም በማሸግ በአንድ ፖስታ ውስጥ አድርጎ ማቅረብና አስመዝግቦ በጨረታ ሳጥን ውስጥ መክተት ይኖርባቸዋል። በቀረበው የጨረታ መመሪያና የጨረታ ሰነዶች ላይ ካልተፈረመና የድርጅቱ ማህተም ካልተደረገበት የጨረታ ሰነድ አካል የሆነውን የተጫራቾች መመሪያ እንዳልተቀበሉ በመቁጠር ያቀረቡት የጨረታ ሰነድ ከጨረታ ውጪ ወይም ውድቅ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው መሸነፋቸው ከተገለፀላቸው ጊዜ ጀምሮ ያስያዙት CPO ወዲያውኑ ሲመለስላቸው አሸናፊዎች ግን ውል ከተፈራረሙና የውል ማስከበሪያ ዋስትና ገንዘብ ካስያዙ በኋላ ተመላሽ ይሆናል።
- ማንኛውም ተጫራች የተጠቀሰውን መስፈርት ያላሟላ ሰነድና ከላይ የተቀመጠውን እቃ ሳምፕል (ናሙና ያላቀረበ እንደሆነ ከጨረታው ውጪ ይሆናል፡፡
- አንድ ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከጫፌ ካራቡ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ፣ ንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት የሥራ ሂደት ክፍል የቢሮ ቁጥር 05 በአካል በመቅረብ የአንድ ጥቅል (Lot) የጨረታ ሰነድ ዋጋ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ::
- ጨረታው የሚከፈተው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ 15 የሥራ ቀናት አየር ላይ ይቆይና በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ታሽጎ በዚሁ ዕለት በ4:15 ጫፌ ከራቡ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ፣ ንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት የሥራ ሂደት ክፍል የቢሮ ቁጥር 05 ጨረታው ይከፈታል፡፡
- 16ኛው ቀን ከሥራ ቀን ውጪ ቅዳሜ ወይም እሁድ ቀን ላይ የሚውል ከሆነ ሰኞ ዕለት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ:-
በሸገር ከተማ አስተደደር የፉሪ ክ/ከተማ የጨፌ ከረቡ ወረዳ
ገንዘብ ጽ/ቤት ያገኙናል።
ለበለጠ መረጃ : የስልክ ቁጥር 09172589/0925406931
በሸገር ከተማ አስተደደር የፉሪ ክ/ከ የጨፌ ከረቡ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት