Addis Zemen (Oct 15, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር ኢሱስ/003/2019
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በ2019 በጀት ዓመት ለሠራተኞች የደንብ ልብስ አገልግሎት የሚውሉ ብትን ጨርቅ፣ የወንድ ጫማ፣ የሴት ጫማ፣ ሴፍቲ ጫማ፣ ሸሚዝ፣ የዝናብ ልብስ፣ የሱፍ ካፖርት፣ የጽዳት ሽርጥ፣ ቱታ እና ልዩ ልዩ የደንብ ልብሶችን በግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ አቅራቢ ድርጅቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች ሁሉ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ ጥቅምት 17 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ ለዚህ ሥራ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ስም በተከፈተ የባንክ ሒሳብ ቁጥር 1000004652782 ገቢ በማድረግ ዋናውን ማስረጃ በማቅረብ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።
ተጫራቾች በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ስም የጨረታ ማስከበሪያ ብር 250,000.00 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ጋራንቲ በማስያዝ ዋናውን ማስረጃ ከጨረታ መወዳደሪያ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
ተጫራቾች በስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርኘራይዝ ልማት ጽ/ቤት ውስጥ የተደራጁ ህጋዊ ጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራት በጨረታው ለመወዳደር የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ያለባቸው ከአደራጃቸው ተቋም የሚያቀርቡት የድጋፍ ደብዳቤ ውስጥ መካተት ያለባቸውሁኔታዎች የሚወዳደሩበትን ተቋም ስም፣ የሚወዳደሩበትን የግዥ ዓይነት፣ የጨረታ ቁጥር እና የጨረታ ማስከበሪያውን የገንዘብ መጠን በግልጽ በአሃዝና በፊደል የተፃፈ የድጋፍደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው።
ተጫራቾች የቴክኒካልና ፋይናንሻል የመጫረቻ ሰነዶችን የያዘ አንድ ዋና እና አንድ ቅጂለየብቻው በፖስታ በማድረግና በጽሑፍ በመለየት የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር የምስክር ወረቀት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያገለግል ከሊራንስ፣ የመንግስትግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት፣ የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈፀም ቃል የሚገባበት ቅፅ እና የጨረታማስከበሪያውን በታሸገ ፖስታ በማድረግ የመጫረቻ ሰነዶቻቹሁን አሟልታችሁ እስከ ጥቅምት 17 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀው የጨረታሳጥን ውስጥ ገቢ ማድረግ አለባቸው።
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ጥቅምት 17 ቀን 2019 ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ፒያሳ ጣይቱ ሆቴል አጠገብ በሚገኘው የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ዋና መ/ቤት ይከፈታል።
አገልግሎቱ ስለጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታወን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-126-7816 ደውሎ መረዳት ይቻላል።
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት