የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል ኪው ማናጅመንት ሲስትም አቅርቦት ዝርጋታ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል ኪው ማናጅመንት ሲስትም አቅርቦት ዝርጋታ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Oct 18, 2026)

በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ማስታወቂያ 02/2019

የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን ኪው ማናጅመንት ሲስትም አቅርቦት ዝርጋታ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ፡፡

ሎት1. ኪው ማናጅመንት ሲስትም አቅርቦት ዝርጋታ

በዚሁ መሠረት 1-

  1. በየዘርፉ የታደስ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው ፣ የዘመኑን ግብር የገበረ
  2. የቫት (VAT) ተመዝጋቢነት ሰርተፊኬት ያለው
  3. የግብር ከፋይ /TIN/ መለያ ቁጥር ያለው
  4. የዕቃና የአገልግሎት አቅራቢነት ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶች
  5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፊ ከተራ ቁጥር 1- 4 የተጠቀሰውን ማስረጃዎች ኦርጅናልና ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ለያንዳንዱ ሎት ሰነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በሲዳማ ክልል ገቢዎች ባለስልጣን በተከፈተው አካውንት ቁጥር 1000347602028 በማስገባት እስልፒ ይዞ ሲዳማ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቢሮ ቁጥር 230 በመቅረብ ሠነዱን መውሰድ ይቻላል፡፡
  7. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት የጨረታ ዋጋ ማስከበሪያ በCPO / በBid Bond የ90 ቀን/ወደም ብር 15,000/አስራ አምስት ሽህ/ በጠቅላይ ፍርድ ቤት ስም በማሰራት ማቅረብ የሚችል፡፡ 
  8. ተጫራቾች የፋይናሻል ዶክመንት ኦርጂናል 1 እና 2 ኮፒ በተለያየ በሰም በታሸገ ኢንቬሎፕ ለጨረታ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ መክተት ይኖርባቸዋል እንዲሁም ቴክኒካል ዶክመንት ኦርጂናል 1 እና ኮፒ በተለያየ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ተከታታይ 15 ቀናት ቅዳሜና እሁድ ጨምሮ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች  ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ዕለቱ በዓል / የስራ ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተገለጸው ስዓት ይከፈታል፡፡
  10. የጨረታ አሸናፊ ዕቃውን በራሱ ወጪ አጔጉዞ መጋዝን ማስገባትና ሰነዱ ላይ በተገለጸው መሰረት አገልግሎቱን ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  11. የጨረታው አሸናፊ በጨረታ መመሪያ መሠረት የጨረታ አሸናፊነቱ በማስታወቂያ ይገለጻል ፡፡

መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ
መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 046 212 5584/0913 175 091
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍርድ ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *