Addis Zemen (Oct 20, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የየካ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በመደበኛ ግልጽ ጨረታ ቁጥር 001/2019 ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች መስፈርቱን ከሚያሟሉ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅቶች ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል::
- ሎት 1- አላቂ የቢሮ እቃዎች ግዥ
- ሎት 2 – የጽዳት እቃዎች ግዥ
- ሎት 3- የሕትመት ውጤቶች ግዥ
- ሎት 4 – የሥራና ደንብ ልብስ እና ተዛማጅ እቃዎች ግዥ
- ሎት 5 ልዩ ልዩ የአይን መነጽር ግዥ
- ሎት 6- የአይቲ እና የኤሌክትሪክ እቃዎች ግዥ
- ሎት 7 – የሕንፃ መሣሪያዎች እቃዎች ግዥ
- ሎት 8 – የተሽከርካሪዎች መለዋወጫ እቃዎች ግዥ
- ሎት 9 – የጀነሬተር ሰርቪስ እና ጥገና
- ሎት 10 – የፕሪንተር መለዋወጫ እቃዎች ግዥ
- ሎት 11 – የተሽከርካሪ ወንበር ፤ ጠረጴዛና ተዛማጅ እቃዎች ጥገና ግዥ
- ሎት 12- የካውንተር ሥራ
- ሎት 13 – የምንጣፍ ሥራ እና የመጋረጃ ስራ ከነተዛማጅ እቃዎች ጋርና ከነእጅ ዋጋው
- ሎት 14 – የታሸገ ውሃ ግዥ
- ሎት 15 – ገብስ ቆሎ ኦቾሎኒ እና ሽንብራ ድብልቅ ግዥ
1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
2.ተጫራቾች በዕቃ አቅራቢነት የተመዘገቡ ፣ በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ እንዲሁም በ2019 ዓ.ም በጨረታ መሳተፍ የሚችሉ ለመሆናቸው ከሚመለከተው ግብር ሰብሳቢ መ/ቤት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና በዳግም ምዝገባ የተመዘገቡ፣
3.ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ በጨረታ ሰነዱ ላይ በየሎቶቹ ለጨረታ ማስከበሪያ የተቀመጠውን ገንዘብ መጠን በመመልከት በምትወዳደሩበት ሎት የተቀመጠውን ገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /CPO/ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የየካ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት ስም በማስያዝ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባችሁ፣
4. ተጫራቾች የሚጫረቱባቸውን እቃዎች ዓይነት ለመለየት የሚያስችል እቃዎች ስፔስፍኬሽን ከጨረታ ሰነድ ጋር ተያይዞ ቢቀርብ ይመረጣል፣
5. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ 15% ታክስን ያካተተ መሆን አለበት፣
6. በሁሉም ሎቶች በአንድ ኢንቨሎፕ ፋይናንሺያል ኦርጅናልና ኮፒው በዝርዝር ተሞልቶ ኦርጅናልና ኮፒውን ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ድረስ ለዚሁ ጨረታ ሲባል በተዘጋጀው ሳጥን ቢሮ ቁጥር 502 ማስገባት አለባቸው::
7. የጨረታው ሳጥን ማስታወቂያ በወጣ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 4:00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ እለት በ4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 5ኛ ፎቅ ላይ ቢሮ ቁጥር 502 ይከፈታል፣
8. የተጠቀሰው ቀን በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፣
9. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300 /ሦስት መቶ ብር/ ክፍያ በመፈፀም የጨረታ ሰነዱን 5ኛ ፎቅ ላይ ቢሮ ቁጥር 502 መውሰድ ይችላሉ ፣
10. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች 7ኛ ፎቅ ቅ/ጽ/ቤቱ መጋዘን ወይም ስቶር ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለበት ፣
11. ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
አድራሻ፦
መገናኛ ከ22 ታክሲ መያዣ ዝቅ ብሎ አማረ አብርሃምና ቤተሰቦቹ ህንፃ 5ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 502 ነው ::
ለማንኛውም ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ የስልክ ቁጥር 011 668 42 07 ደውላችሁ መጠየቅ ትችላላችሁ::
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የየካ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት