Addis Zemen (Oct 20, 2026)
የግልጽ ጨረታ
ማሰታወቂያ ቁጥር ዐ1/2019
በአብክመ በምስራቅ ጎጃም ዞን የአነደድ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለወረዳ ባለበጀት መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ
- ሎት.1 የእህል ምርት ውጤቶች አስከ ሰኔ 30/2019 ዓ/ም የሚቆይ የኮንትራት ውል አቅርቦት፤
- ሎት 2 የምግብ እህሎች አስከ ሰኔ 30/2019ዓ/ም የሚቆይ የኮንትራት ውል አቅርቦት፤
- ሎት 3 አትክልትና ፍራፍሬ አስከ ሰኔ 30/2019 ዓ/ም የሚቆይ የኮንትራት ውል አቅርቦት፤
- ሎት 4 የመኪና ዘይትና ቅባት፤
- ሎት 5፤የፍትህ ጽ/ቤት የቢሮ ጥገና CG/ BC 7 እና በላይ ያላቸውን
- ሎት 06 የአፈር ግድብ ስራ አገልግሎት የሚውል ኤከስካቫተር ከነደርሶ መልስ ሎቬዱ ኪራይና ናፍጣና ሌሎች ወጭዎችን ተጫራቹ ችሎ ፤
- ሎት ዐ7 የተለያዩ የመኪና እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ/ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፤የስራ ተቋራጭ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት፤ የግብር ከፍያ የምስክር ወረቀትና የንግድ ስራ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- የግዥ መጠኑ ከብር 500000.00/አምስት መቶ ሽህ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /የቫት ከፋይነት/ የምስከር ወረቀት ማቀረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና ሌሎች ማስረጃዎች ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዞ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዛውን እቃ ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን ከመጫረቻ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከሎት01 እስከ ሎት ዐ4 እና ሎት 6ና ሎት 7 ያሉትን ለእያንዳንዱ ሎት ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/ ሎት05 300.00/ሶስት መቶ ብር በመቤታችን የገቢ ደረሰኝ በመሂ 1 ገቢ በማድረግ ሰነዱን መግዛት ይችላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድ ቦንድ ለሚወዳደሩበት ጥቅል ዋጋ
- ለሎት1 እና ሎት 2 በቆይታ ጊዜው የሚገዛውን መጠን ታሳቢ ያደረገ ለእያንዳንዱ 20000.00 /ሃያ ሽህ ብር/
- ለሎት 3. በቆይታ ጊዜው የሚገዛውን አትከልትና ፍራፍሬ መጠን ታሳቢ ያደረገ 5000.00/ አምስት ሽህ አምስት ብር፤ ለሎት 4. 7500.00/ ሰባት ሽህ አምስት መቶ ብር/፤
- ሎት 5. 20000.00/ሃያ ሽህ ብር/
- ሎት 6. 10000.00/አስር ሽህ ብር/
- ሎት 7. 5000.00/አምስት ሽህ ብር/ ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንከ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት በማስያዝ ሰነዱን አያይዞ ማቅረብ አለበት፡፡
- ከተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ጸንቶ መቆያ ጊዜ የጨረታዋጋ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ቢያንስ ለተጨማሪ 28 ቀናት ጸንቶ መቆየት አለበት።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ሰሙን፤ ፊርማውንና ማህተሙን በማሳረፍ ከሎት 01 እስከ ሎት 04 እንዲሁም ሎት 6 እና ሎት 7 የሚወዳዳሩ ተወዳዳሪዎቸ ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ10ተከታታይ ቀንና እስከ 11ኛው ቀን 3፡30 ድረስ አነደድ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ማስገባት ያለበት ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን 3፡30 ታሽጎ 4፡30 ላይ ይከፈታል፡፡ በሎት 05 የሚወዳደሩ ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 20 ተከታታይ ቀንና እስከ 21ኛው ቀን 3፡30 ድረስ የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ስሙን፤ ፊርማውንና ማህተሙን በማሳረፍ አነደድ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት አለበት፡፡ ጨረታው በ21ኛው ቀን 3፡30 ታሽጎ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጨረታ መክፈቻ ሰዓቱ ባይገኙም መ/ቤቱ ጨረታውን የመክፈት መብት ያለው ሲሆን በጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት ያልተገኙ ተወዳዳሪዎች በተላላፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡
- በጨረታ ሰነዱ ላይ የማብራሪያ የማሻሻያ ጥያቄን በተመለከተ ከሎት oı እስከ ሎት 04 እና ሎት 6 እና 7 ያሉት ጨረታው ሊዘጋ 5 ቀናት እስኪቀረው እንዲሁም ለሎት 05 ደግሞ ለመጫረቻ ሰነድ ማቅረቢያ የተወሰነው ጊዜ ሊያበቃ 10 ቀናት እስኪቀረው ድረስ ለሚቀርብ የማሻሻያ ወይም የማብራሪ ጥያቄ ብቻ ይሆናል፡፡
- አሸናፊው አካል ያሸነፈባቸውን እቃዎች ጠቅላላ ወጭውን በመሸፈን ከሎት01 እስከ ሎት o3 ድረስ ያሉትን ሎጀስቲክና የሎጀስቲከ ግብዓቶችን ውል ከያዘበት ቀን ጀምሮ እንዲያቀርብ በተጠየቀ በ3 ቀናት ውስጥ አነደድ ወረዳ አምበር ከተማ የሚያቀርብ ሲሆን ለሎት 04 እና ሎት 7 ደግሞ ውል ከያዘበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በ15 ቀናት አስተዳደር ፑል ንብረት ከፍል ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡ ፡ በሎት 05 አሸናፊ የሆነው አካል ደግሞ ውል ከያዘበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 60/ስልሳ ቀናት ውስጥ የቢሮ ጥገና ግንባታውን ጨርሶ ማስረከብ ይኖርበታል፡፡ በሎት6 አሸናፊ የሆነው አካል ደግሞ ውል ከያዘበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በ100 ሰዓት የአፈር ግድብ ስራውን ማጠናቀቅ አለበት ፡፡በአጠቃላይ ለሁሉም ሎቶች ለውል መያዣ የሚፈለጉ ወጭዎችን አሸናፊው አካል የሚሸፍን ሲሆን ግዥ ፈጻሚው መ/ቤት ከሎት o5 ውጪ ላሉት ግዥዎች ቅድሚያ ክፍያ አይሰጥም፡፡በጨረታው ለወጡት ሎቶች ሙያ የሚጠይቁ እቃዎች ደግሞ በሚመለከተው ባለሙያ ተረጋግጠው ገቢ ይሆናል፡፡ ግዥ ፈጻሚው አካል ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን በጨረታው መሰረዝ ምክንያት ለወጣው ወጭ ግዥ ፈጻሚው አካል ተጠያቂ አይሆንም፡፡
- ከሎት ዐ5 ውጭ ላሉት ግዥዎች ውድደሩ የሁሉም ሎቶች በጥቅል ዋጋ ስለሚታይ ተጫራቾች በአንድ ሎት ያሉትን ዝርዝር እቃዎች ሁሉንም ዋጋ መሙላት አለባቸው :: ግዥ ፈጻሚው አካል ካወጣው ስፔስፊኬሽን ውጭ በራሱ ስፔስፊኬሽን የሞላ ተወዳዳሪ ከውድድርውጭ ይሆናል፡፡መ/ቤቱ በሎት 4፤ሎት 6፤ና በሎት 7 የሚገዛቸውን እቃዎች መጨመር ወይም መቀነስ ቢፈልግ 20% መጨመር ወይም መቀነስ መብት አለው፡፡
- በማንኛውም ግዥ ለእቃዎች ከብር 20,000.00/ሃያ ሽህ በላይ፤ ለአገልግሎት ግዥ ደግሞ 10,000.00/አስር ሽህ ብር በላይ ለሚሆኑ ግዥዎች አቅራቢው ከሚፈጸምለት ከፍያ ላይ 3% ቅድመ ግብር/ዊዝ ሆልድ ተቀንሶ የሚቀር ሲሆን በውል አፈጻጸም ወቅት የዋጋ ማስተካከያ ማድረግ አይፈቀድም ፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ አነ/ወ/ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 03 በአካል ወይም በስልከ ቁጥራችን 0913271823 /0946088403/0920120967/0920503640 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአነደድ ወረዳ ገዘብ ጽ/ቤት