በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ/የሐዋርያው ጴጥሮስ ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም የበጀት ዓመት ለትምህርት አገልግሎት የሚውል ቋሚ ዕቃዎች፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ አላቂ የትምህርት ዕቃዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ ህትመት፣ ካፌና መስተንግዶ፣ አይ ሲቲ ጥገና እና የደንብ ልብሶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ/የሐዋርያው ጴጥሮስ ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም የበጀት ዓመት ለትምህርት አገልግሎት የሚውል ቋሚ ዕቃዎች፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ አላቂ የትምህርት ዕቃዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ ህትመት፣ ካፌና መስተንግዶ፣ አይ ሲቲ ጥገና እና የደንብ ልብሶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Oct 23, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/2019

በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ/የሐዋርያው ጴጥሮስ ት/ቤት ለ2019ዓ.ም የበጀት ዓመት ለትምህርት አገልግሎት የሚውል ቋሚ ዕቃዎች፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ አላቂ የትምህርት ዕቃዎች የፅዳት ዕቃዎች፣ ህትመት፣ ካፌና መስተንግዶ፣ አይ ሲቲ ጥገና እና የደንብ ልብሶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም ተጫራቾች፡-

1.የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑ ግብር የከፈሉ፣ በመ/ግ/ን/አስ/የዕቃ አቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ

2. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት በየሎቱ የማይመለስ 500.00 (አምስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።

3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ (0.5-2)% በእያንዳንዱ ሎት በተበጀተለት በጀት መሰረት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

  • ካፌና መስተንግዶ ሎት 001– 8,448.00ብር
  • የፅዳት እቃዎች ሎት 002- 8,912.00ብር
  • አላቂ የቢሮ እቃ ሎት 003–14,615.00ብር
  • አላቂ የት/ት እቃ ሎት 004–12,180.00ብር
  • ህትመት እቃ ሎት 005 4,320.00ብር
  • ቋሚ የቢሮ እቃዎች ሎት 006–7,500.00ብር
  • የደንብ ልብስ ሎት 007-36,117.00 ብር
  • አጠቃላይ አይ.ሲ.ቲ ጥገና ሎት 008-7,500.00ብር

4. ተጫራቾች የሚያቀርቧቸውን የጥራት ደረጃና ለአስተማማኝነቱ ለእያንዳንዱ እቃ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና ማስገባት ይኖርባቸዋል።

5. ጨረታው አየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ሆኖ በ10ኛው ቀን 11፡30 ይታሸጋል። በ11ኛው ቀን 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ነገር ግን ቀኑ የሕዝብ በዓል እንዲሁም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን 4፡30 ላይ ይከፈታል።

6. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ድርጅት በተመረጠው ናሙና መሰረት ዕቃዎችን ትምህርት ቤት ድረስ ማምጣት እና ማስረከብ ይኖርባቸዋል።

7. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ:- ወረዳ 06 ጎፋ ገብርኤል ዝቅ ብሎ ወደ ጎፋ ካፕ በሚወስደው መንገድ (ከመስቀል ክትፎ በስተጀርባ ገባ ብሎ ቀበሌ 52 ፊት ለፊት)

ለበለጠ መረጃ 011 466 1878
በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ/የሐዋርያው
ጴጥሮስ ት/ቤት