Addis Lessan (Oct 24, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የልደታ ከፍለ ከተማ የወረዳ 9 ፋይናንስ ጽ/ቤት በጨረታ ቁጥር ል/ክ/ከ/ወ/9/ፋ/ጽ/ቤት/01/19 አላቂ የቢሮ እቃወች፣ የደንብ ልብስ፣ የፅዳት እቃዎች፣ የትራንስፖርት አገልግሎት፣ የመድረክ ዲኮርና ሙሉ ሳውንድ ሲስተም አገልግሎት፣ ኤሌክትሮኒክስ ጥገና፣ ቋሚ እቃዎች የመኪና እቃዎች፣ የቢሮ እቃዎች ጥገና፣ ለስላሳ መጠጦች እና ምግቦች፣ የእንቁላል ጣይ ዶሮ እና የአትክልት ዘር ግዥ በግልጽ ጨረታ መግዛት እና በውል ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
1. በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
2. ተጫራቾች በገንዘብ ሚኒስተር በእቃ አቅራቢነት ዝርዝር በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ እንዲሁም በ2019 ዓ.ም በጨረታ መሳተፍ የሚችሉ ለመሆናቸው ከሚመለከተው ግብር ሰብሳቢ አካል የተሰጣቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በአጠቃላይ የእቃወች ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ (CPO) በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም በማስያዝ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ
- (ሎት 1)፦ የፅህፈት መሳሪያ 18000 (አስራ ስምንት ሺ ብር)
- (ሎት 2)፦ አላቂ የቢሮ እቃዎች 4000 (አራት ሺ ብር )
- (ሎት 3)፦ የፅዳት እቃዎች 10000 (አስር ሺ ብር)
- (ሎት 4)፦ የደንብ ልብስ 39000 (ሰላሳ ዘጠኝ ሺ ብር)
- (ሎት 5)፦ ቋሚ እቃዎች/የመኪና እቃዎች 20000 (ሃያ ሺ ብር)
- (ሎት 6)፦ የመድረክ ዲኮርና ሳውንድ ሲስተም 2000 (ሁለት ሺ ብር)
- (ሎት 7)፦ የትራንስፖርት አገልግሎት 2000 (ሁለት ሺ ብር)
- (ሎት 8)፡– የኤሌክትሮኒክስ ጥገና 2000 (ሁለት ሺ ብር)
- (ሎት 9)፡– የቢሮ እቃዎች ጥገና 2000 (ሁለት ሺ ብር)
- (ሎት 10)፡– የቢሮ መስተንግዶ ውሃና ምግቦች 2000 (ሁለት ሺ ብር)
- (ሎት 11)፡– የቄብ እንቁላል ጣይ ዶሮና የአትክልት ዘር 2000 (ሁለት ሺ ብር)
4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከወረዳ 9 ፋይናንስ ጽ/ቤት አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 401 በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
5. ተጫራቾች የሚጫረቱባቸውን እቃዎች አይነት ለመለየት የሚያስችል ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ ከአንድ ቀን በፊት ማቅረብ አለባቸው ናሙና ለማይቀርብላቸው እቃወች ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ መቅረብ አለበት፡፡
6. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ በታሸገ ኢንቨሎፕ ኦሪጅናልና ኮፒ በማድረግ ማስታወቂያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ጨረታ ሲባል በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ቢሮ ቁጥር 401 ማስገባት አለባቸው፡፡
7. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ 15% ታክስን ያካተተ መሆን አለበት ካላካተተ እንደተካተተ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
8. የጨረታው ሳጥን ማስታወቂያ በወጣበት 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተዘግቶ በአስራ አንደኛው ቀን በ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 401 ይከፈታል፡፡ ዕለቱ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
9. በጥቃቅን እና አነስተኛ ተደራጅተው ለሚወዳደሩ አምራች ከሆኑ ለአምራችነታቸው የተሰጣቸውን ማስረጃ ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን መወዳደር የሚችሉት በተደራጁበት ዘርፍ ብቻ መሆን አለበት፡፡
10. ወረዳው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡
አድራሻ፡– ባልቻ ሆስፒታል ከፍ ብሎ ሶሊያና ህንጻ ፊት ለፊት
ስልክ ቁጥር፡– 011 869 3713 / 011 059 5404
በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ፋይናንስ ጽ/ቤት