Reporter (Oct 25, 2026)
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
ቁጥር ሲባ/ህአዲ ሐራጅ/04/2019
ሲንቄ ባንክ አማ በአዋጅ ቁጥር 97/1990(እንደተሻሻለው) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ቀጥሎ የቀረቡትን ንብረቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የተበዳሪ ስም |
የንብረት አስያዥ ስም |
አበዳሪ ቅርንጫፍ
|
ለጨረታ የቀረበው ንብረት መግለጫ |
የጨረታ መነሻ ዋጋ በብር |
ጨረታው የሚከናወንበት |
ጨረታው የወጣው
|
||||
|
ለጨረታ የቀረበው ንብረት |
ከተማ ክ/ከተማ/ቀበሌ/ወረዳ የቤት ቁጥር |
የካርታ ቁጥር
|
የቦታ ስፋት
|
ቀን |
ሠዓት |
||||||
|
1 |
ፍቃዱ እና መስፍን የብረታብረት ስራ ኃላ/የተ/የግል ማህበር |
ፍቃዱ እና መስፍን የብረታብረት ስራ ኃላ/የተ/የግል ማህበር |
አዳ |
ለመኑፋክቸሪንግ ኣገልግሎት የሚያገለግል መጋዘን |
ሽገር ከተማ ገላን ክ/ከተማ ገላን ቀበሌ |
BMG/K/L/I/FM/2013
|
3000 ካ.ሜ
|
63,172,717
|
17/2/2019
|
4:30-6:00
|
ለ2ኛ ጊዜ |
|
አዳ |
ለመኑፋክቸሪንግ ኣገልግሎት የሚያገለግል መጋዘን |
ሽገር ከተማ ገላን ክ/ከተማ ገላን ቀበሌ |
BMG/K/L/I/H-B.M.A/2013
|
3000 ካ.ሜ
|
63,991,166.08
|
17/2/2019
|
8:00-9:30
|
ለ2ኛ ጊዜ |
|||
|
3 |
ዳግማዊት ሲዩም ሉምባሶ
|
በቀለች ሞገስ ማናግደዉ
|
ሀርቡ
|
የጋራ መኖሪያ ቤት
|
አዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ወረዳ 10 (አራብሳ የጋራ መኖሪያ ቤት |
AA0000610073132670216 |
53.52ካ.ሜ
|
2,245,610
|
18/2/2019 |
4:30-6:00 |
ለመጀመሪያ ግዜ |
የሐራጁ ደንቦች
1. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪል የጨረታውን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ (1/4ኛ) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ.) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ። አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በአሥራ አምስት (15) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካል ከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል። በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል።
2. በሐራጁ ሂዳት ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበው ተጫራች ማን እንደሆነ ብቻ የሚገለፅ ሲሆን ጨረታውን ያሸነፈው ሰው አካል ስለማሸነፉ በሚመለከተው የባንኩ አካል ከተረጋገጠ በኃላ ማሸነፉን የሚገልጽ ደብዳቤ ይሰጠዋል።
3. ላላሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ በዕለቱ ይመለስላቸዋል።
4. በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ ተበዳሪ እና ንብረት አስያዥ ወይም ሕጋዊ ተወካዮች ብቻ ናቸው።
5. ሐራጁ የሚካሄድበት ቦታ ካዛንቺስ የሚገኘዉ ሲንቄ ባንክ ዋና መስሪያ ቤት 7ኛ ፎቅ ይሆናል።
6. ለስም ዝውውር የሚከፈል ክፍያ እንዲሁም የሊዝ እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ክታክስ እና ግብር ጋር ተያያዥ የሆኑ ክፍያዎችን ገዢው አሸናፊው ጨረታውን ከአሸነፈበት ጊዜ ጀምሮ ይከፍላል።
7. የንግድ ማህበራትን በመወከል መጫረት የሚፈልግ ማንኛዉም ግለሰብ የማህበሩን ህጋዊ ሰዉነት ያለዉ መሆኑን የሚያረጋግጥ የመመስረቻ ወይም እና የመተዳደሪያ ደንብ እንዲሁም ህጋዊ የዉክልና ስልጣን ሰነድ ይዞ መቅረብ ይጠበቅበታል።
8. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
9. ለሐራጅ የቀረበ ንብረቶችን ለመጎብኘት የሚፈልግ ከአበዳሪ ቅርንጫፉ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ መጎብኘት ይቻላል።
10. ተጫራች የጨረታ አሸናፊ ነዉ የሚባለዉ አሸናፊነቱን የሚገልፅ ደብዳቤ በፅሑፍ ሲደርሰዉ ነዉ።
11. ለተጨማሪ መረጃ የሲንቄ ባንክ ህግ አገልግሎት ክፍል ስልክ ቁጥር (+251-11 557-6016) ፤ ኦዳ ቅርንጫፍ (011 557 1965) እና ሀርቡ ቅርንጫፍ 011 557 8781 ላይ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
ሲንቄ ባንክ አ.ማ