አሐዱ ባንክ አ.ማ የንግድ ህንጻ የቦታ ስፋት 440 ካ.ሜ (G+1) የሆነ የጎግል ካርታ ኮርድኔት ቁጥር 8.542174, 39.267697 በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

አሐዱ ባንክ አ.ማ የንግድ ህንጻ የቦታ ስፋት 440 ካ.ሜ (G+1) የሆነ የጎግል ካርታ ኮርድኔት ቁጥር 8.542174, 39.267697 በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Reporter (Oct 25, 2026)

የሐራጅ ማስታወቂያ

ቁጥር-28/2019

አሐዱ ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 97/190 (እንደተሻሻለው) በተሰጠው ስልጣንና ውክልና መሠረት ቀጥሎ የቀረበውን ንብረት በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ተ.ቁ

የተበዳሪው ስም

የመያዣ ሰጪ ስም

አበዳሪ ቅርንጫፍ

 

ለሐራጅ የቀረበው ንብረት ዝርዝር መግለጫ

የሐራጅ

መነሻ ዋጋ

በብር

ሐራጁ የሚከናወንበት

ሐራጁ

የወጣው

 

 

ቀን

ሰዓት

 

 

የንብረቱ አይነት

አድራሻ

 

የካርታ ቁጥር

የቦታ ስፋት

 

1

ቢኤስ ቢ ዲ ትሬዲስንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

አቶ ሳሙኤል በለው መኮንን

መስቀል አደባባይ

 

የንግድ ህንጻ የጎግል ካርታ ኮርድኔት ቁጥር 8.542174, 39.267697

ኦሮሚያ ክልል፣ አዳማ ከተማ፤ ቀበሌ 06

525/03

 

440 ካ.ሜ (G+1)

 

34,017,651

 

ህዳር 16 ቀን 2019 ዓ.ም

 

ከ4:00-5:00

 

ለመጀመሪያ ጊዜ

 

 

የሐራጅ ደንቦች፡–

1. ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ (1/4ኛ) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ.) ብቻ በአሐዱ ባንክ አ.ማ ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።

2. አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ አሸናፊ መሆኑ በደብዳቤ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ባሉት በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃልሉ መክፈል አለበት። ካልተከፈለ የተያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል።በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃሉ። በጨረታው ተሸናፊ ለሆኑት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ በዕለቱ ይመለስላቸዋል።

3. በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ ተበዳሪ እና ንብረት አስያዥ ወይም ሕጋዊ ተወካዮቻቸው ብቻ ናቸው።ተበዳሪ እና ወኪሎቻቸው ባይገኙም ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል።

4.የጨረታ አሸናፊ ለሆነው ተጫራች በባንኩ የብድር ፖሊሲ፣ መመሪያ እና ቅደመ ሁኔታ መሠረት እስከ 70 በመቶ የሚደርስ ብድር ሊመቻች ይችላል።

5.የተጫራቾች ምዝገባ ከእያንዳንዱ የንብረት ሐራጅ መዝጊያ ሰዓት ከሰላሳ ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል። በሐራጁ የመጨረሻ ሰላሳ ደቂቃዎች የተጫራች ምዝገባ አይካሄድም።

6.የሐራጁ አሸናፊ ገዢ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን፣ ከስም ማዛወሪያ ክፍያ ጋር የተገናኙ እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ የግብር ግዴታዎችን ገዥው አሸናፊው ይከፍላል።

7.ተጫራቾች የጨረታው ቀን ከመድረሱ 5 (አምስት) ቀን በፊት ከባንኩ ጋር በመነጋገር በስራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ በቦታው በመገኘት ለጨረታ የቀረበውን ንብረት መጎብኘት ይቻላል።

8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታው አሸናፊ ነው የሚባለው አሸናፊነቱን የሚገልፅ ደብዳቤ በፅሑፍ ሲደርሰው ነው።

9. ጨረታው የሚከናወነው በአሐዱ ባንክ አማ አዳማ ቅርንጫፍ ውስጥ ነው።

10. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 526 0223 (ሕግ አገልግሎት መምሪያ) ደውለው መጠየቅ ይችላሉ::

አሐዱ ባንክ አ.ማ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *