በአብክመ የከሚሴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለከሚሴ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት የወጥ ቤት እቃዎች (ሎት 1) እና የኮንስትራክሽን እቃዎች (ሎት 2) ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በአብክመ የከሚሴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለከሚሴ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት የወጥ ቤት እቃዎች (ሎት 1) እና የኮንስትራክሽን እቃዎች (ሎት 2) ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Oct 28, 2026)

የወጥ ቤት እቃዎች እና የኮንስትራክሽን እቃዎች ግዥ

ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ 

በአብክመ የከሚሴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለከሚሴ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት የቡኡረ ቦሩ ቁጥር 1 እና ቁጥር 2 ቅድመ መደበኛ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተማሪዎች ምገባ ለማስጀመር ለመመገቢያ እና ለምግብ ማብሰያ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች እንዲሁም የ02 አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2019 ዓ.ም የመማሪያ ክፍል እጥረት ስላጋጠመ ጊዜያዊ የመማሪያ ክፍል ግንባታ ቆርቆሮ በቆርቆሮ ለመስራት የሚያስፈልጉ የኮንስትራክሽን እቃዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት 1 የወጥ ቤት እቃዎች
  • ሎት 2 የኮንስትራክሽን እቃዎች

ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ ፍቃደኛ የሆኑ

1. ለስራው ህጋዊ ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ ለስራው የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፤ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው ግዥው ከ500,000 በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆነ።

2. የጨረታው ሰነድ ከከሚሴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 7 በግዢ/ፋይ/ንብ/አስ/ዋና የስራ ሂደት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ከላይ የተዘረዘሩትን መረጃዎች ዋናና ኮፒ በመያዝ ዘወትር በስራ ቀንና ሰዓት ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ የኢትዮ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነድን መውሰድ ይችላሉ።

3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋና እና ኮፒ በማድረግ በታሸገ ኤንቨሎፖች በአብክመ የከሚሴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በግዢ/ፋይ/ንብ/አስ/ዋና የስራ ሂደት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ አስረኛ (10) ቀን ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ ባለው ጊዜ ማስገባት ይችላሉ።

4. ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስራ አንደኛ (11) ቀን ማለትም በቀን 30/2/2019 ዓ.ም 4፡30 ላይ በግዢ ፋይ/ንብ/አስ/ዋና የስራ ሂደት ቢሮ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

5. ተጫራቾች ተመላሽ የሚደረግ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሎት 1 3,000 (ሶስት ሺህ ብር) እንዲሁም ለሎት 2 3,000 (ሶስት ሺህ ብር) በባንክ ትእዛዝ /CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ማስያዝ አለባቸው።

6. የጨረታ አሸናፊ የሆነው ድርጅት ውል በሚዋዋልበት ጊዜ የውለታ ማስከበሪያ ከአጠቃላይ ድምር ዋጋ 10% በባንክ ትእዛዝ /CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ማስያዝ ይኖርበታል።

7. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

8. ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ፤ በከሚሴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በግንባር በመቅረብ ወይንም በስልክ ቁጥር 033 554 0144 ደውለው መረዳት ይችላሉ።

የከሚሴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *