Addis Zemen (Oct 29, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
በፍርድ ባለመብት ጌትነት ኃ/ሚካኤል እና በፍርድ ባለዕዳ በሽር ገመቹ መካከል ያለውን የአፈጻጸም ክርክርን አስመልክቶ በአዳማ ከተማ ድሬ ነጋ ወረዳ ውስጥ የሚገኘው መኖሪያ ቤት የካርታ ቁጥር 5012/2008 የሆነ እና በፍርድ ባለዕዳ ስም የተመዘገበ የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር 19,671,893.00 (አስራ ዘጠኝ ሚሊዮን ስድስት መቶ ሰባ አንድ ሺህ ስምንት መቶ ዘጠና ሶስት ብር) የሆነ መግዛት የሚፈልግ አካል ግልጽ በሆነ ጨረታ በ21/03/2019 ከ3፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ቤቱ በሚገኝበት ቦታ የጨረታ ኮሚቴ መግዛት የሚፈልጉ ሰዎችን ድርጅትን አወዳድሮ የሚሸጥ መሆኑን እየገለጸ መግዛት የሚፈልግ ቀርቦ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
1. የጨረታ – ማስታወቂያ አየር ላይ የሚቆየው ለተከታታይ ቀናት ከ19/02/2019 እስከ 19/03/2019 በአዳማ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ በሉጎ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ፣ በአዳማ ከተማ አስተዳደር ፊት ለፊት፣ ቤቱ በሚገኝበት እና በከለቻ ኦሮሚያ ጋዜጣ እና በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ለ30 ቀናት የሚቆይ ይሆናል።
2. መግዛት የሚፈልግ ሰው/ድርጅት/ የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር 19,671,893.00 (አስራ ዘጠኝ ሚሊዮን ስድስት መቶ ሰባ አንድ ሺህ ስምንት መቶ ዘጠና ሶስት ብር) 25 ፐርሰንት ሲፒኦ በባንክ በማስያዝ ማስረጃ ማቅረብ አለበት።
የአዳማ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፍታሐብሔር ጉዳይ ችሎት