Addis Zemen (Oct 29, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ለእስቴሽነሪና ለጽዳት እቃዎች ግዥ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የይርጋ ጨፌ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት በግልጽ ጨረታ አወዳድረው ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- 1ኛ ሎት እስቴሽነሪ / የጽህፈት መሳሪያዎች
- 2ኛ ሎት የጽዳት እቃዎች
ይህ ጨረታ በዘርፉ አግባብ ያለው የታደሰ የንግድ ፍቃድ ፤የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው፡፡ የተጨማር እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ከታክስ ክሊራንስ ማቅረብ ለሚችሉት ተጫራች ሁሉ ክፍት ነው፡፡
1. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ለጽህፈት መሳሪያዎች ሎት 5000 ብር ለጽዳት እቃዎች ሎት 2500 ብር በኢትዮጵያ ከታወቀው ባንክ ሲ.ፒ.ኦ ወይም ጥሬ ገንዘብ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይችላል፡፡
2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ መግዣ ብር 300 /ሶስት መቶ/ የማይመለስ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ተኛው ቀን ዘወትር በስራ ሰዓትይ/ጨ/ከ/ግ/ን/ አስተዳደር ቢሮ በመቅረብ መግዛት ይችላል፡፡
3. ጨረታው የሚቀርበውና የሚፈጸመው በወኪል ከሆነ ከሚመለከተው ውክልና ሰጪ/ መዝጋቢ አካል የተሰጠ ህጋዊ ውክልና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
4 ተጫራች ለሚያቀርቡት እቃ የነጠላና የጠቅላላ ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ በመሙላት ዋናና ሁለት ኮፒ በታሸገ ፖስታ የተጫራች ንግድ ድርጅት ማህተም ተደርጎበትና ተፈርሞ ይ/ጨ /ከ/ፋ/ግ/ን/ አስተዳደር ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ይህ ማስታወቅያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ተኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በመንግስት በስራ ቀን ብቻ ማስገባት ይቻላል፡፡
5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በተራ ቁጥር 4 በተገለጸው ቢሮ በግልጽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ጨረታው የሚከፈተው 16ተኛው ቀን የመንግስት የስራ ቀን ካልሆነ ወይም በበዓል ዝግ ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል፡፡
6 ተጫራች ባይገኝም በሌሉበት የሚከፈት ይሆናል፡፡
7 ከተጠቀሰው ሰዓት ዘግይቶ የሚመጣዉ የመወዳደሪያ ሀሳብ ወይም ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
8 ተጫራቾች አሸናፊ ከሆኑ ለይርጋጨፌ ከተማ ፋይናንስ እቃዎችን ውል በገባበት ጊዜ ገደብ ውስጥ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡ የማጓጓዣ ወጭ በከተማ ፋይናንስ የሚሸፈን ይሆናል፤
9. የከተማው ፋይናንስ ጽ/ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡ 09 12 063 953
የይርጋ ጨፌ ከተማ
አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት