በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ 112ኛ ኮማንዶ ክፍለ ጦር የተለያዩ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ 112ኛ ኮማንዶ ክፍለ ጦር የተለያዩ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Oct 30, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ የግዥ መለያ

ቁጥር የ12ኛ ኮ/ክ/ጦር ግ.ጨ 01/2019

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ 112ኛ ኮማንዶ ክፍለ ጦር ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት አንድ አላቂ የፅህፈት ዕቃዎች እና የፅህፈት ማቴሪያሎች
  • ሎት ሁለት አላቂ የቢሮ የፅዳት ዕቃዎች እና የህሙማን ማገገሚያ
  • ሎት ሦስት ለቀላል ተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎች
  • ሎት አራት የህንፃ መሳሪያዎች እና ለወታደራዊ ተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎች

ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ድርጅቶች

1. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ዕቃ በዘርፉ ቀጥተኛ ተዛማጅ ያለው በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) የምስክር ወረቀት እና የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ሚ/ር ባወጣው የዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡበትን/ የዕቃ አቅራቢነት ምስክር ወረቀት የዘመኑን የስራ ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።

2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል ገንዘብ ለእያንዳንዱ ሎት በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ/CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ብቻ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማስገባት አለባቸው።

3. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00/አንድ መቶ ብር/ ለአንድ ሎት በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታውጆ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ ባሉት ቀናት ወንዶጢቃ ማለትም ከጥቁር ውሃ ወደ ሓዋሳ ኤርፖርት በሚወስደው መንገድ 8 ኪ/ሜ ርቀት ላይ በሚገኘው ካምፕ ፋይናንስ ቢሮ በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰንድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጥቅምት 2 ቀን 2019 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ህዳር 04 ቀን 2019 ዓ/ም እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ግዥ ዴስክ ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

5. ጨረታው ህዳር 24 ቀን 2019 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመስሪያ ቤቱ በግዥ ቢሮ ውስጥ ይከፈታል።

6. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር 112ኛ ኮማንዶክፍለ ጦር


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *