ከጠቅላላው ይዞታ ስፋት በፕሮፖርሽን ከግቢው ለቤቱ የሚደርሰው 362.46 ካ/ሜ የሆነ ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ – test3.diretenders.com

ከጠቅላላው ይዞታ ስፋት በፕሮፖርሽን ከግቢው ለቤቱ የሚደርሰው 362.46 ካ/ሜ የሆነ ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ


Addis Zemen (Oct 30, 2026)

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመበት ዮሀንስ በቀለ እና በፍ/ባለዕዳ እነ ኤደን ገብረክርስቶስ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.120502 በሚያዝያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም እና የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.123172 በ25/09/2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ለአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 06 የቤት ቁጥር 774 የካርታ ቁጥር 13/07/1/9250 በእነ ሙሉ እመቤት በቀለ ብርቄ ስም የተመዘገበ ከጠቅላላው ይዞታ ስፋት በፕሮፖርሽን ከግቢው ለቤቱ የሚደርሰው 362.46 ካ/ሜ ቤቱ ያረፈበት 164.59 ካ/ሜ የሐራጅ መነሻ 21,877,993.30 (ሃያ አንድ ሚሊዮን ስምንት መቶ ሰባ ሰባት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰላሳ ሶስት ብር ከ30/100) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 25 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ በ4፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ CPO የሚያመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነው አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ቤት ስም CPO በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሰርተው ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሀራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 11 273 0852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *