የቦታ ስፋት 139 ካ/ሜ የሆነ ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ – test3.diretenders.com

የቦታ ስፋት 139 ካ/ሜ የሆነ ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ


Addis Zemen (Oct 30, 2026)

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት ዘውድነሽ እንዳለ እና የፍ/ባለዕዳ የሸዋጌጥ ታደሰ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል መጀመሪያ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 22706 በ30/8/2018 ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/24770 በ17/10/2018 ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/24770 በ01/11/2018 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 08 የቤት ቁጥር አዲስ ይዞታ መለያ ቁጥር AA000100804671 በእነ የሸዋጌጥ ታደሰ ደስታ (3 ሰዎች) ስም የተመዘገበ እና በሊዝ ስሪት የሚተዳደር የቦታ ስፋት 139 ካ/ሜ የሆነ ቤት ቤቱ ያረፈበት 43.34 ካ/ሜ የሆነ በግቢው ውስጥ ያለው ሌላ መኖሪያ ቤት ግድግዳ አንድ እና ያልተለየ ሲሆን ይዞታው 19.34ካ/ሜ መንገድ የሚነካው ሆኖ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 3,090,190 (ሦስት ሚሊዮን ዘጠና ሺህ አንድ መቶ ዘጠና) ሆኖ የትራንዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ኅዳር 22 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 4፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሦስት የሥራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO አሠርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በሕጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 112 730 852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *