የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት መንገዶች ባለሥልጣን ዋና መ/ቤት በተለያዩ ፕሮጀከቶች እና ጥገና ጽ/ቤቶች ለሚያከናውናቸው የመንገድ ግንባታ እና ጥገና ሥራ አገልግሎት የሚውል ሎደር (ሎት 1) እና ሲኖትራክ ገልባጭ መኪና (ሎት 2) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት መንገዶች ባለሥልጣን ዋና መ/ቤት በተለያዩ ፕሮጀከቶች እና ጥገና ጽ/ቤቶች ለሚያከናውናቸው የመንገድ ግንባታ እና ጥገና ሥራ አገልግሎት የሚውል ሎደር (ሎት 1) እና ሲኖትራክ ገልባጭ መኪና (ሎት 2) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል


Addis Zemen (Oct 29, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር ደ/ም/መ/ባ/06/2019

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት መንገዶች ባለሥልጣን ዋና መ/ቤት በተለያዩ ፕሮጀከቶች እና ጥገና ጽ/ቤቶች ለሚያከናውናቸው የመንገድ ግንባታ እና ጥገና ሥራ አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የተዘረዘሩ

  •  በሎት 1 ሎደር እና
  • በሎት 2 ሲኖትራከ ገልባጭ መኪና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል፡፡

ሎት

የማሽን/

ተሽከርካሪ/ዓይነት

የማሽን /ተሽከርካሪ/ፈረስ ጉልበት

የማሽን/ ተሽከርካሪ/ የመጫን አቅም በሜ.ኩ

የሥሪት ዘመን

እ.ኤ.አ

የሚጠቀመው

የነዳጅ ዓይነት

 

ለአንድ ማሽን

ተሽከርካሪ/ የሚፈለገው ሰዓት/ወር

ብዛት በደስትሪክት

 

ቦርጋ

ታርጫ

ሚዛን

1

ሎደር

150 እና በላይ

3

2018 እና በላይ

ናፍጣ

1000 ሰዓት

 

1

1

1

2

ሲኖ ትራክ ገልባጭ መኪና

336 እና በላይ

14

2020 እና በላይ

ናፍጣ

7 ወር

8

8

8

 በዚሁም መሰረት ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ዝርዝር መሰረት አቅራቢዎችን ይጋብዛል፡-

  1. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችለውን የዘመኑን ግብር የተከፈለበትን ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ የንግድ ሥራ ፊቃድ ወይም የአገልግሎት ሥራ ፈቃድ፣ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት፡ ተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የንግድ ምዝገባ ሰረተፍኬት ፡ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN NO) እና በጨረታ ለመሳተፍ ከሀገር ውስጥ ገቢ ቢሮ የድጋፍ ደብዳቤ ከጨረታ ሰነዳቸዉ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል ፡፡
  2. ተጫራቾች ዋጋቸዉን በታሸገ ኤንቨሎፕ የፋይናንሻል እና ቴክኒካል ፕሮፖዛሉን በተለያዬ ፖስታበማድረግ አንድ ዋና እና ሁለት ኮፒ ‹‹ኦርጅናል›› እና ‹‹ኮፒ›› በማለት እና የጨረታ ማስከበርያዉንም ለእያንድንዱ ሎት በተለያዬ ፖስታ ለየብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በባለስልጣን መ/ቤቱ የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000642058936 ገቢ በማድረግ የባንክ ደረሰኝ በመያዝ ከባለስልጣን መ/ቤቱ ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ኬዚ ቲም ቢሮ መዉሰድ ይችላሉ፡፡
  4. የጨረታዉ አሸናፊ የሚወስነዉ በጨረታ ሰነዱ ዉስጥ በተመለከቱት መስፈረቶች መሰረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛዉም አቅራቢ ክፍት ነዉ፡፡
  5. አቅራቢዎች ጨረታውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ገቢ የሚያደርጉበት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛ ቀን ሲሆን ጨረታዉ ከቀኑ 11፡30 ድረስ ይሆናል፡፡ ጨረታዉ ሎት 1 በ16ኛ ቀን ከጧቱ 3፡00 ተዘግቶ በዕለቱ ጧት 3፡30 ሎት 2 ከቀኑ 8፡ዐዐ ተዘግቶ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል ፡፡ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) ለሎት 2 200,000(ሁለት መቶ ሺህ ብር) በቅድሜ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና፡በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲፕኦ (CPO) ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ከዚህ ውጭ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም፡
  7. ተጫራቾች በጨረታዉ ደንብና መመሪያ መሰረት ጨረታቸዉን ማቅረብ አለባቸዉ ከጨረታ ደንብና መመሪያ ዉጭ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለዉም ::
  8. ተጫራቾች ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ በተመሳሳይ ዘርፍ ከሰሩበት የመንግስት መ/ቤት ቢያንስ አንድ የመልካም ስራ አፈፃፀም ከጨረታ ሰነዳቸዉ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል::
  9. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በክፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ

በምዕራብ ኦሞ ዞን ጀሙ ከተማ በሚገኘዉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት

መንገዶች ባለስልጣን ዋና መ/ቤት በግብዓት አቅርቦትና አስተዳደር ዘርፍ ግዥና ንብረት አስተዳደር

ኤዚ ቲም ቢሮ በአካል በመቅረብ ማነጋገር ወይም በስልክ ቁጥር 0474527941 /0474527727 ደውለዉ ማነጋገር ይቻላል::

ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት መንገዶች ባለስልጣን ዋና መ/ቤት

ምዕራብ ኦሞ ዞን

ጀሙ ኢትዮጵያ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *