በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን አዳሚ ቱሉ የፀረ-ተባይ ማዘጋጃ ፋብሪካ የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን አዳሚ ቱሉ የፀረ-ተባይ ማዘጋጃ ፋብሪካ የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Oct 31, 2026)

በድጋሚ የወጣ ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር APPF/NCB/03/19

1. በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን አዳሚ ቱሉ የፀረ–ተባይ ማዘጋጃ ፋብሪካ ከዚህ በታች የተገለፁትን የተለያዩ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

  • LOT.1. የሰራተኞች የደንብ ልብስ
  • LOT 2 . የሠራተኞች የስራ ቦታ ደኅንነት መጠበቂያ መሳሪያዎች (PPE)
  • LOT. 3 የፅዳት እቃዎች
  • LOT 4. የፅህፈት መሳሪያ እቃዎች
  • LOT. 5. የተለያዩ ተሽከርካሪ ጎማዎች

2. ተጫራቾች የስራ ዘርፍ የሚያሳይ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ለሚከፈልባቸው ዕቃዎች የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ በመንግሥት የግብር ሕግ መሠረት ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያሳይ ሰርቲፊኬት እና በመንግሥት ግዥ ለመሳተፍ በመንግስት የኤሌክትሮኒክ ሥርዓት ፖርታል ላይ በአቅራቢነት መመዝገቡን የሚያሳይ መረጃ እንደ ቅድመ ሁኔታ ማቅረብ ይኖባቸዋል።

3. ተጫራቾች አዳሚ ቱሉ ባለው የፋብሪከው ዋና መስሪያ ቤት ወይም አዲስ አበባ ቦሌ ሩዋንዳ ከኩዌት ኤምባሲ 10 ሜትር ገባ ብሎ ጅቡቲ ኤምባሲ ፊትለፊት ከሚገኘው ማስተባበሪያ ቢሮ የማይመለስ ብር አምስት መቶ ብቻ (500.00) በመክፈል ጨረታው ማስታወቂያ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።

4. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ የተጫራቹ ድርጅት ስምና አድራሻ በትክክል ተጽፎ የድርጅቱ ማህተም ያረፈበት መሆን ይኖርበታል።

5. ተጫራቾች ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ሰነዶቻቸውን ኮፒ እና ኦርጅናሉን በተለያየ በሰም በታሸገ ኤንቬሉፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

6. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት እቃ በራሳቸው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመሙላት በተጫራቹ ድርጅት ኃላፊ ተፈርሞና ማህተም በማድረግ ማቅረብ አለባቸው።

7. ተጫራቾች ለጨረታ ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን አዳሚ ቱሉ የፀረ–ተባይ ማዘጋጃ ፋብሪካ ስም የባንክ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከጨረታው የቴክኒካል ሰነድ ጋር ለብቻው በፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው።

8. ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሰነዱን እስከ ህዳር 01 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 7፡00 ድረስ የፋብሪከው ዋና መስሪያ ቤት ወይም አዲስ አበባ በሚገኘው ማስተባበሪያ ቢሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ መክፈቻው እለት ህዳር 01 ቀን 2010 ዓ.ም ከቀኑ 7፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ አበባ ቦሌ ርዋንዳ በሚገኘው ማስተባበሪያ ቢሮ ይሆናል።

9. ፋብሪካው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፡– አ.አ ማስተባበሪያ ስልክ ቁጥር ቁጥር 011 662 4656 አ/አ

አዳሚ ቱሉ 046 441 9164(ማዞሪያ)፣ 046 441 9287 (ንግድ መምሪያ)

ፖ.ሣ.ቁ 1206 (አ.አ)፣ 247 (አ/ቱሉ)

በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን አዳሚ ቱሉ የፀረ– ተባይ ማዘጋጃ ፋብሪካ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *