Addis Zemen (Oct 31, 2026)
የአማካሪ አገልግሎት የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/2019
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ፅ/ቤት በክፍለ ከተማው ሊያስገነባቸው የፈለገውን ግንባታዎች የአፈር ምርመራ ስራ ሀገር በቀል አማካሪዎችን አወዳድሮ በማዋዋል ለማሰራት ይፈልጋል።
በመሆኑም ተጫራቾች ለስራው አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን፣ የሰው ሀይል በተጨማሪም የሚቀጥሉትን መስፈርቶች በማሟላት የጨረታ ሰነዱን አንድ ብቻ መውሰድ ይችላሉ።
- ሎት1. ገላን ጉራ 2ተኛ ደረጃ ጂ+4 ት/ቤት፤ ወረዳ 10 ወጣት ስብዕና ማዕከል ግንባታ፤ወረዳ 13 ጂ+5 ጤና ጣቢያ ግንባታ፤ወረዳ 2 ጂ+4 ፖሊስ ጣቢያ ግንባታ
- ሎት2. ህብረት ችቦ 1ኛ ደረጃ ጂ+4 ት/ቤት፤ እውቀት ወጋገን 1ኛ ደርጃ ጂ+4 ት/ቤት፤ኢትዮ ኮርያ 2ተኛ ደረጃ ጂ+4 ቁጥር 1 ት/ቤት፤ኢትዮ ኮርያ 2ተኛ ደረጃ ጂ+4 ት/ቤት ቁጥር 2፤ ወረዳ 7 ቃሊቲ ጂ+5 ጤና ጣቢያ ግንባታ
1. ደረጃቸው በአፈር ጥናትና ምርመራ ደረጃ 4 እና ከዛ በላይ የሆኑ
2. ለስራው የአገልግሎት ጊዜው ያላለፈ(የታደሰ) ህጋዊ የስራ ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ ብቻ(ለጨረታ መሳተፍ የሚያስችል)፣ ከኮንስትራክሽን ቢሮ የልዩ ለአፈር ጥናት ስራ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው ፣ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው መጫረት ይችላሉ(የታደሱ)።
3. የጨረታ ሰነዱን ከአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ፅ/ቤት 2ተኛ ፎቅ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ ባሉ አስራ አምስት የስራ ቀናት ከላይ የተዘረዘሩትን ዋናና ኮፒ በመያዝ ዘወትር በስራ ቀንና ሰዓት የማይመለስ ብር 1000 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
4. ተጫራቾች የጨረታውን
ሀ. ቴክኒካል ሰነድ አንድ ዋና እና ሁለት ኮፒ
ለ. ፋይናንሺያል ሰነድ አንድ ዋና እና ሁለት ኮፒ በማድረግ በታሸገ ኤንቨሎፕ እንዲሁም ሁሉንም ሰነዶች በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ 7ኛ ፎቅ አዳራሽ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ እስከ አስራ ስድስተኛው የስራ ቀን የጨረታ መመሪያው በሚያዘው መሰረት በዚሁ ዕለት የጨረታ ሰነዱን (Technical and Financial) ሁሉንም ሰነዶች በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ ባለው ጊዜ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች የፕሮጀክቱን ስም፣ የድርጅታቸውን ስያሜ እና እርጥብ ማህተምና ፊርማ ሁሉም ፖስታዎች ላይ ማስፈር እና ኦርጅናሉ ላይ ኦርጅናል፣ ኮፒዎቹ ላይ ኮፒ በማለት መጻፍ ያለባቸው ሲሆን ይህን አለማድረግ ከውድድር ያሰርዛል። ጨረታው በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ 7ኛ ፎቅ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የቴክኒካል ጨረታ ሰነድ ይከፈታል።
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (bid bond) 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንከ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በባንክ ዋስትና በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ፅ/ቤት ስም ማስያዝ አለባቸው። የሚያስይዙትንም (CPO) ወይም የባንክ ዋስትና ከቴክኒካል ኦሪጂናል ዶክመንት ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
6. በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ስራ ያላቸው የስራ ተቋራጮች በክ/ከተማው ጨረታ ለመሳተፍ የያዙትን ስራ ከ 70% በላይ ማድረሳቸውን መረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
7. የጨረታውን መመሪያ አለማክበር እና ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች አለማሟላት ከተወዳዳሪነት ያሰርዛል።
8. ከአንድ ሰነድ በላይ መወዳደር ከተወዳዳሩበት ሁሉ ላይ ያሰርዛል ፤ በተጨማሪም ተጫራቾች ሞልተው ያስገቡት ሰነድ በሁሉም ገፆች ላይ ማህተም እና ፊርማ አለማድረግ፣ የስራ ዝርዝር ዋጋ (Rate) ላይ የማይነበብ እና ስርዝ ድልዝ ካለ ፣ ዋጋ (Rate) ያልተሞላበት የስራ ዝርዝር እንዲሁም የስራ ዝርዝር ዋጋ (Rate) ላይ ፍሉድ መጠቀም ከተወዳዳሪነት ያሰርዛል።
9. የበለጠ ማብራሪያ ካስፈለገ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ፅ/ቤት በአካል በመቅረብ መረዳት ይቻላል።
10. አድራሻ፡– ከቃሊቲ መናኸሪያ ፊት ለፊት በሚገኘው አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ህንጻ ላይ ሁለተኛ ፎቅ የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ፅ/ቤት የምህንድስና ግዢ ቡድን።
11. ልዩ አማካሪው ጨረታውን ካሸነፉ በኋላ ቢያንስ የሰራተኛውን 40% በክፍለ ከተማው የተመዘገበ ስራ አጥ ባለሙያ ወይም መሃንዲስ መቅጠር አለበት። ለዚህም መተማመኛ በድርጅቱ ሃላፊ ወይም ስራ አስኪያጅ የተፈረመና ማህተም ያለው ደብዳቤ የሚያቀርብ ማረጋገጫ ደብዳቤ ማቅረብ አለበት።
12. አማካሪው ድርጅት የዲዛይን ሀሳብ(footing type suggestion) ያቀርባል።
13. አማካሪ ድርጅቱ ሥራውን በጥራት ለማከናወን የሚከተላቸውን መሰረታዊ ስትራቴጂዎች የሚያቀርብና እነዚህም ባለመፈጸማቸው ተጠያቂ እንደሚያደርገው ማረጋገጫ የጻፈና በስራ አስኪያጅ ወይም በሃላፊው የተፈረመና ማህተም ያለው ሰነድ የሚያቀርብ።
14. ልዩ አማካሪው በደረጃው እንዲያሟላ የሚጠበቅበትን የሰው ሃይል ያለውና በህጋዊ መንገድ በክፍለ ከተማችን የተመዘገቡ ባለሙያዎችን የሚቀጥር መሆኑን የሚገልጽ ሰነድ እንዲሁም ፕሮጀክቱን በጥራት ለማከናወን በቴክኒክ ሰነዱ ላይ አስፈላጊ ናቸው የተባሉ ባለሙያዎችን በወቅቱ እንደሚያሟላ በድርጅቱ ሃላፊ ወይም ስራ አስኪያጅ የተፈረመና ማህተም ያለው ደብዳቤ የሚያቀርብ
15. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ፅ/ቤት