በማእከላዊ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ጉብሬ ዲስትሪክት ጽ/ቤት በሥሩ ለሚገኙ ፕሮጀክቶች እና ጥገና መስመሮች አገልግሎት የሚውሉ የውሀ ቦቴ፣ ለሰርቪስና ነዳጅ ማመላለሻ የሚሆን አይሱዙ ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በማእከላዊ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ጉብሬ ዲስትሪክት ጽ/ቤት በሥሩ ለሚገኙ ፕሮጀክቶች እና ጥገና መስመሮች አገልግሎት የሚውሉ የውሀ ቦቴ፣ ለሰርቪስና ነዳጅ ማመላለሻ የሚሆን አይሱዙ ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 01, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ጉብሬ ዲስትሪክት 001/2019

በማእከላዊ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ጉብሬ ዲስትሪክት ጽ/ቤት በሥሩ ለሚገኙ ፕሮጀክቶች እና ጥገና መስመሮች አገልግሎት የሚውሉ የውሀ ቦቴ ፤ ለሰርቪስና ነዳጅ ማመላለሻ የሚሆን አይሱዙ ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል።

1. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስፈልጋቸውን የዘመኑን ግብር የተከፈለበትን ከሚፈለገው አገልግሎት የተዛመደ የንግድ ስራ ፈቃድ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት እና በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

2. ተጫራቾች ዋጋቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ የፋይናንሻል ፕሮፖዛሉን በተለያየ ፖስታ በማድረግ አንድ ዋና << ኦሪጅናል ›› እና አንድ ፎቶ ኮፒ በማለት እና የጨረታ ማስከበሪያውን በተለየ ፖስታ ለብቻው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች ሰነዱን የማይመለስ ብር 50.00 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል ከዲስትሪክቱ ጽ/ቤት የቢሮ ቁጥር 4 መውሰድ ይችላሉ።

4. የጨረታው አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሰረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም አቅራቢ ክፍት ነው።

5. አቀራቢዎች ጨረታውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ገቢ የሚያደርጉበት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 6፡00 ድረስ ይሆናል። ጨረታው በዚያኑ ቀን ከቀኑ 8፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል። ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።

6. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 1% የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከዚህ ውጪ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም።

7. ተጫራቾች በጨረታው ደንብና መመሪያ መሠረት ጨረታቸውን ማቅረብ ለለባቸው፣ ከጨረታው ደንብና መመሪያ ውጪ የሚቀርብ ማንኛውም ጨረታ ተቀባይነት የሰውም።

8. ዲስትሪከቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣፣

ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፣ የጉብሬ ዲስትሪክት ጽ/ቤት

ስልክ ቁጥር 011 322 0325 / 011 322 0327 / 011 322 0328

በማእከላዊ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ጉብሬ ዲስትሪክት ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *