Addis Zemen (Nov 01, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የሸገር ከተማ አስተዳደር የኮዬ ፈጬ ከፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ መሰረተ ልማት የሚሰሩ ማሸነርዎች እና ትናንሽ መኪናዎችን ለመከራየት ይፈልጋል።
ስለዚህ ከዚህ በታች የተገለጸውን መመሪያ መረጃዎች በማቅረብ/ ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ፍቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ።
2. በአቅራቢዎች ዝርዝር ተርታ የተመዘገቡና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ ምስክር ወረቀት ያላቸው፤
3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት (15) ተከታታይ የስራ ቀናት ስለ ጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 1500.00 (አንድ ሺህ አምስ መቶ) ብር በኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት በመክፈል ሰነዱን ከኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት መውሰድ ይችላሉ።
4. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር (ሰነድ) ዋና እና ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ (በፖስታ) በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት (15) ተከታተይ ቀናቶች ድረስ በኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጸ/ቤት ባዘጋጀውየጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይቻላል።
5. ጨረታው በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥን ታሽጎ (ተዘግቶ) ልክ በዚሁ ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ ቤት ውስጥ ይከፈታል። ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል። ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የማይገኙ ከሆነ ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም።
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ/ CPO/ ብቻ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማስያዝ ይኖርባችኋል።
7. ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊነቱ ከተገለፀላቸው በኋላ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መዋዋልይጠበቅባቸዋል።
8. ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለፀላቻው በኋላ በተገለፀላቸው ቀን ቀርበው ውል ካልፈፀሙና የውል ማስከበሪ ካላስያዙ የጨረታ ማስከበሪያው ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
9. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለጹትን ማንኛውንም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለሁ ማለት አይችልም።
10. የመወዳደሪያ ሰነዱ በጨረታ በተዘረዘረው መሠረት ተሞልቶ መቅረብ ይኖርበታል።
11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኝ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ፡– በስልክ ቁጥር 011 439 9493 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
በሸገር ከተማ አስተዳደር የኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ / ቤት