Reporter (Nov 01, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፦ 001
ንስር ማይክሮፋይናንስ ተቋም አ.ማ. በአዲስ አበባ ከተማ ለሚያስገነባው የቢሮ ሕንፃ ዲዛይን ለማዘጋጀት ብቃት ያላቸውን የምድብ 1 (Category-1) የሥነ–ሕንፃና ምህንድስና አማካሪ ድርጅቶችን በጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
1. የተጫራቾች ብቃት መስፈርቶች
በኢትዮጵያ ሕጋዊ በሆነ መንገድ የተቋቋሙና የሚከተሉት ሰነዶች ያሏቸው ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
- የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ማረጋገጫ፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ማረጋገጫ፤
- ተጫራቹ በማንኛውም የመንግሥት ጨረታ ላይ ለመሳተፍ ብቁ መሆኑን የሚገልጽና ቢያንስ እስከ ጨረታ ማቅረቢያ የመጨረሻ ቀን ድረስ የሚያገለግል የግብር ክሊራንስ ምስክር ወረቀት፣
- ከሚመለከተው አካል የተሰጠ የታደሰ የምድብ 1 (Category-1) የሥነ–ሕንፃና ምህንድስና አማካሪ የምዝገባ ምስክር ወረቀት።
2. የጨረታ ሰነድ ስለማግኘት
ተጫራቾች ከጨረታው ማስታወቂያ ቀን ጀምሮ እስከ ህዳር 11 ቀን 2019 ዓ.ም. ድረስ የማይመለስ የጨረታ ሰነድ መግዣ ክፍያ ብር 2,000.00 (ሁለት ሺህ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ።
ክፍያው በንስር ማይክሮፋይናንስ ተቋም አ.ማ. በሚገኘዉ እና በንስር ማይክሮፋይናንስ ተቋም አ.ማ. ስም በተከፈተዉ ሂሳብ ቁጥር 1005192501 ገቢ መደረግ አለበት።
ተጫራቾች የተከፈለበትን የክፍያ ደረሰኝ ቅጂ ከዚህ በታች በተጠቀሰው ኢሜይል አድራሻ መላክ ይኖርባቸዋል:: የጨረታ ሰነዱም በኢሜይል ይላክላቸዋል።
3. የጨረታ ዋስትና
እያንዳንዱ ተጫራች ብር 300,000.00 (ሶስት መቶ ሺህ ብር) የጨረታ ዋስትና በCPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ እና የማይሻር የባንክ ዋስትንስ (Unconditional and Irrevocable Bank Guarantee) ማቅረብ አለበት።
በኢንሹራንስ የተሰጡ ዋስትናዎችና በሁኔታ ላይ የተመሰረቱ ዋስትናዎች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
4. የጨረታ ሰነድ ማቅረቢያና መክፈቻ
የጨረታ ሰነዶች በተለያዩ የታሸጉ ፖስታዎች መቅረብ አለባቸው።
እነዚህም፦
1. የቴክኒክ ፕሮፖዛል (Technical Proposal)፤
2. ዋጋ ማቅረቢያ (Financial Offer)፤
3. የጨረታ ዋስትና (Bid Security) ናቸው።
ፖስታዎቹ በአንድ የውጭ ፖስታ ውስጥ ተደርገው መታሸግ አለባቸው።
ዋና ሰነድ (ORIGINAL) እና ተጨማሪ ቅጂዎች (COPIES) በግልጽ ሁኔታ መለየት አለባቸው።
የጨረታ ሰነዱ እስከ ህዳር 14 ቀን 2019 ዓ.ም. ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ በንስር ማይክሮፋይናንስ ተቋም አ.ማ. ዋና መሥሪያ ቤት፣ አዲስ አበባ መቅረብ አለበት።
ጨረታው በዚያው ቀን ከቀኑ 9፡30 ሰዓት በንስር ማይክሮፋይናንስ ተቋም አ.ማ. ዋና መሥሪያ ቤት በጨረታ መክፈቻ ክፍል ይከፈታል።
ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በመክፈቻው ላይ መገኘት ይችላሉ።
5. ለበለጠ መረጃ
አድራሻ፦ ንስር ማይክሮፋይናንስ ተቋም አ.ማ.
ኢሜይል፦ conbid@nisirmfi.com
ስልክ፦ +251 94 731 7445/ +251 95 040 0809
ንስር ማይክሮፋይናንስ ተቋም አ.ማ. ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ ወይም የማሻሻል መብቱ የተጠበቀ ነዉ።