ኦቢኤም ኮንስትራሽን ድርጅት” (OBM Construcion Enterprise) ለዋና መስሪያ ቤት (Head Office) አገልግሎት የሚውል 1 (አንድ) ዘመናዊ ተሽከርካሪ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

ኦቢኤም ኮንስትራሽን ድርጅት” (OBM Construcion Enterprise) ለዋና መስሪያ ቤት (Head Office) አገልግሎት የሚውል 1 (አንድ) ዘመናዊ ተሽከርካሪ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Reporter (Nov 01, 2026)

የጨረታ ቁጥር፡ EV-TENDER PSM003/2019

 “ኦቢኤም ኮንስትራሽን ድርጅት” (OBM Construction Enterprise) ለዋና መስሪያ ቤት (Head Office) አገልግሎት የሚውል1 (አንድ) ዘመናዊ ተሽከርካሪ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

1. ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው ህጋዊ መስፈርቶች

  • በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፤
  • የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እና የቫት (VAT) ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፤
  • ወቅታዊ የመንግስት ግብር የከፈሉበትን ማረጋገጫ (Tax Clearance) ማቅረብ የሚችሉ፤
  • በአቅራቢዎች ዝርዝር (Suppliers List) የተመዘገቡ መሆናቸውን ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፤

2. የዕቃው ዓይነት እና ብዛት በአጭሩ

  • የዕቃው ዓይነት፡– BYD Tang-L– Large SUV 7 seater EV (Hybrid) ወይም ተመጣጣኝ ቴክኒካዊ ብቃት ያለዉ።

ብዛት፡ 1 (አንድ)00 ኪሎሜትር (Zero Kilometer)

3. የጨረታ ሰነድ አቀራረብ እና መመሪያ

  • ተጫራቾች የማይመለስ ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ሜክሲኮ ኮሜርስ ፊት ለፊት በሚገኘው ቢፍቱ ህንፃ 6ኛ ፎቅ ኦቢኤም ኮንስትራክሽ ድርጅት – ፋይናንስ ቢሮ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት በድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) ብር (2%) በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም የባንክ ጋራንቲ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማያያዝ አለባቸው።
  • ተጫራቾች የቴክኒክ እና የፋይናንሻል ሰነዶቻቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦሪጅናል እና አንድ ኮፒ በማድረግ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣ ቀን ጀምሮ በ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ወስጥ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  • ጨረታው ቀን 02/03/2019 ከጠዋት 4፡00 ላይ ተዘግቶ፣ በዛው ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅታችን የስብሰባ አደራሽ ቢሮ ይከፈታል።
  • መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *