የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሸገር ሪጅን ለሥራ ክፍሎቹ እና ለ30 ደንበኞች አገልግሎት ማዕከላት የሚሆኑ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች (ሎት 1) እና የአይሲቲ ዕቃዎች እና ቶነሮች (ሎት 2) በግልፅ ጨረታ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሸገር ሪጅን ለሥራ ክፍሎቹ እና ለ30 ደንበኞች አገልግሎት ማዕከላት የሚሆኑ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች (ሎት 1) እና የአይሲቲ ዕቃዎች እና ቶነሮች (ሎት 2) በግልፅ ጨረታ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 01, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር ኢ/ኤ/አገ/ሸ/ሪ/ግ/ጨ/004/2019

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሸገር ሪጅን በስሩ ለሚገኙ የሥራ ክፍሎች እና ለ30 (ሰላሳ) ደንበኞቹ አገልግሎት ማዕከላት የጽህፈት መሳሪያዎች ፣ የጽዳት ዕቃዎች እና የአይሲቲ ዕቃዎች ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች ላይ ለመግዛት ይፈልጋል።

የዕቃው አይነት

የመዝጊያ ቀን እና ሰዓት

የመክፈቻ ቀን እና ሰዓት

የጨረታ ዋስትና መስከበሪያ

የጽህፈት መሳሪያዎች እና የጽዳት ዕቃዎች (ሎት 1)

ህዳር 3 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት

ህዳር 3 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት

ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ)

የአይሲቲ ዕቃዎች እና ቶነሮች (ሎት– 2)

ብር 250,000.00 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ)

1. ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨ.እ.ታ ሰርተፍኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና ከገቢዎች ባለስልጣን ጽ/ቤት ጨረታ ላይ እንዲሳተፉ የሚል ማስረጃ ያለው በጨረታው መሳተፍ ይችላል።

2. ተጫራቾች የመንግስት ድርጅቶች በሚያወጡት ጨረታ ላይ ለመሳተፍ እንዲችሉ በመንግስት ግዥና ንበረት አስተዳደር ኤጄንሲ https://epg.ppa.gov.et ድህረ ገጽ ላይ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዝቡ መሆን አለባቸው።

3. በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች በማያያዝ መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ዝርዝር ሁኔታው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ይገኛል።

4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ) ለእያንዳንዱ ሎት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000482105592 EEU- ፊንፊኔ ዙርያ ዲስትሪክት በሚለው በመከፈል መውሰድ ይችላሉ።

5. አድራሻ፡– 22 ድንበሯ ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሸገር ሪጅን ሰፕላይ ቼይን ንብረት እና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ።

6. ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን ከላይ በሠንጠረዡ ውስጥ በፀገለጠው መሠረት ሆኖ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ሲፒኦ /CPO/ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Bid Bond) መሆን ይኖርበታል።

7. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል በአንደ ላይ በማድረግ «ኦሪጅናል እና ኮፒ በማለት በተለያየ ፖስታ በማሸግ እና ሁለቱን በአንድ ትልቅ ፖስታ በማድረግ ጨረታ ቁጥር ኢ/ኤ/አ/ሸገ ሪጅ/ግ/ጨ/004/2019 የሚል በማድረግ እስከ ህዳር 03/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ከላይ በተራ ቁጥር 5 ላይ በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚኖርባቸው ሲሆን፤ ጨረታው ህዳር 03/2019 ዓ.ም 4፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል።

8. ጨረታው ከላይ በተገለፀው መሠረት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

9. ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር +251-011-522-6504 መደወል ይችላሉ።

10. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሸገር ሪጅን

አዲስ አበባ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *