Reporter (Nov 01, 2026)
ለንግድ አገልግሎት የሚውሉ የቤት ኪራይ ጨረታ
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ሜክሲኮ አደባባይ በሚገኘው የህንፃው የመጀመሪያ ወለል ለንግድ ሥራ አገልግሎት ማለትም ለባንኮች፣ ለሱፐር ማርኬት፣ ለቡና ምርት መሸጫ፣ ለፋርማሲ፣ ለቡቲክ፣ ለባህላዊ ልብስ፣ ለጌጣጌጥ፣ ለኤሌክትሮኒክስ፣ የምርት ናሙና ሽያጭ እና የመሳሰሉ አገልግሎቶች የሚውሉ የተለያዩ ስፋት ያላቸው ክፍሎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማከራየት ይፈልጋል።
በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ዘወትር በስራ ሰዓት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 16 የማይመለስ ብር 1,000.00 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፣ ለጨረታው አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶች፣ የሚጫረቱበት ዋጋ እና የጨረታ ማስከበሪያ ሁለት በመቶ /2%/ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ቀናት ውስጥ ቢሮ ቁጥር 013 ማቅረብ ይችላሉ። ምክር ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011 551 4005 መደወል ይቻላል
የኢትዮጵያ የንግድና የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት
አዲስ አበባ