የኦሮሚያ ፓይፕ ፋብሪካ ኃ/የተ/የግል ማህበር ከውጭ ሀገር እና ከሀገር ወስጥ ለሚያስገባቸዉ /ለሚገዛቸዉ/ የፋብሪካ ጥሬ ዕቃዎች ህጋዊ መስፈርቶችን የሚያሟላና በዚህ ስራ ላይ የተሰማሩትን አውራጆችን አወዳደረዉ በኮንትራት ማሰራት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የኦሮሚያ ፓይፕ ፋብሪካ ኃ/የተ/የግል ማህበር ከውጭ ሀገር እና ከሀገር ወስጥ ለሚያስገባቸዉ /ለሚገዛቸዉ/ የፋብሪካ ጥሬ ዕቃዎች ህጋዊ መስፈርቶችን የሚያሟላና በዚህ ስራ ላይ የተሰማሩትን አውራጆችን አወዳደረዉ በኮንትራት ማሰራት ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 01, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር OPF/2026/19/003

ድርጅታችን የኦሮሚያ ፓይፕ ፋብሪካ ኃ/የተ/የግል ማህበር ከውጭ ሀገር እና ከሀገር ወስጥ ለሚያስገባቸዉ /ለሚገዛቸዉ/ የፋብሪካ ጥሬ ዕቃዎች ቀጥሎ በተዘረዘረው ሠንጠረዥ መሠረት ህጋዊ መስፈርቶችን የሚያሟላና በዚህ ስራ ላይ የተሰማሩትን አውራጆችን አወዳደረዉ በኮንትራት ማሰራት ይፈልጋል።

ስለሆነም መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ትችላላችሁ።

ተ.ቁ

የጥሬ ዕቃው ዓይነት

መለኪያ

ብዛት

ጭነቱ የሚመጣባቸው ሁኔታዎች

በ20ft ኮንተይነር

በ40ft ኮንተይነር

ያለኮንተይነር ከጂቡቲ ወደብ እና ከሀገር ዉስጥ

1

ኤች ዲ ፒኢ (HDPE PE100 Black

በኩንታል

1

 

 

 

2

ፒቪሲ ሬይዚን (Polyethylene chloride)

በኩንታል

1

 

 

 

3

ካልስየም ካረቦኔት (Calcium Carbonate)

በኩንታል

1

 

 

 

4

ስታብላይዘር (Stabilizer)

በኩንታል

1

 

 

 

5

ካረበን ብላክ (Carbone Black)

በኩንታል

1

 

 

 

ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸዉ ግዴታዎች፡–

1. ህጋዊና በ2019 ዓ.ም. የታደሰ የጫኝና አውራጅነት ፍቃድ ያላችሁና የዘመኑን ግብር የከፈሉና የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፤

2. ቫት፤ ቲን ሠርተፈኬት ማቅረብ የሚችሉ።

3. ህጋዊ የ7ንዘብ መቀበያ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችል፤

4. አንዱን ኩንታል የሚያወርዱበትንና የሚደረድሩበትን ዋጋ ከላይ በሠንጠረዥ በተዘረዘረው መሠረት በኮምፒዩተር የተጸፈ ዋጋ ማቅረብ የሚችሉ፤

5. ጥሬ ዕቃው በሚወርድበትና በሚደረደርበት ወቅት እንዳይፈስና እንዳይባክን ሙሉ ዋስትና መውስድ የሚችሉ፤

6. ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 2,000.00 (ሁለት ሽህ) በሲፕኦ (CPO) Oromia pipe factory PLC በሚል ማስያዝ የሚችሉ።

በመሆኑም ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች ከላይ የተዘረዘሩትን የፋብሪካ ጥሬ ዕቃዎችን የምታወርዱበትና የምትደረድሩበትን ዋጋ በታሸጋ ኤንቨሎፕ በማቅረብ መወዳደር ትችላለችሁ። ጨረታዉ ህዳር 4 ቀን 2019 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ ወዲያውኑ በ8፡00 ሰዓት ተጨራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በግልጽ የሚከፈት ሲሆን ባይገኙም ያስገቡት የጨረታ ሰነድ ሌሎች ተጫራቾች በተገኙበት ተከፍቶ የሚታይ ይሆናል።

ማሳሰቢያ፡ ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።

አድራሻ፤ ቃሊቲ አሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ፊት ለፊት የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ቅጥር ግቢ በጀርባ በኩል፤

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር– 011 439 5828 / 011 439 5911

የኦሮሚያ ፓይፕ ፋብሪካ ኃ/የተ/የግል ማኅበር


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *