የውኃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ዋናው መ/ቤት) የድሬድዋ ከተማ እና አሌሊቱ ማረሚያ ቤት ጉድጓድ ቁፋሮና ንፁህ ዉሃ መጠጥ አቅርቦት ፕሮጀክቶችን በንዑስ ተቋራጭ የአገልግሎት ግዥዉን ህጋዊ ከሆኑ ድርጅቶች በአገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ Drilling, Construction and Pumping Test of 500+20% Meter 1 (one) Deep Production Water Well, Drilling, Construction and Pumping Test of 350+20% Meter 1 (one) Deep Production Water Well አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። – test3.diretenders.com

የውኃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ዋናው መ/ቤት) የድሬድዋ ከተማ እና አሌሊቱ ማረሚያ ቤት ጉድጓድ ቁፋሮና ንፁህ ዉሃ መጠጥ አቅርቦት ፕሮጀክቶችን በንዑስ ተቋራጭ የአገልግሎት ግዥዉን ህጋዊ ከሆኑ ድርጅቶች በአገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ Drilling, Construction and Pumping Test of 500+20% Meter 1 (one) Deep Production Water Well, Drilling, Construction and Pumping Test of 350+20% Meter 1 (one) Deep Production Water Well አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።


Addis Zemen (Nov 01, 2026)

የጨረታ ጥሪ

ሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ

የጨረታ ቁጥር NCB WWር 02/2019

የውኃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ዋናው መ/ቤት) የድሬድዋ ከተማ እና አሌሊቱ ማረሚያ ቤት ጉድጓድ ቁፋሮና ንፁህ ዉሃ መጠጥ አቅርቦት ፕሮጀክቶችን በንዑስ ተቋራጭ የአገልግሎት ግዥዉን ህጋዊ ከሆኑ ድርጅቶች በአገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ በጨረታ ቁጥር NCB WWc 02 2019 አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ አቅራቢዎች የሚከተሉትን ህጋዊ ሁኔታዎች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ።

ተ.ቁ

የሎት ቁጥር

ዋና ዋና የዕቃ ዝርዝር/ዓይነት Summery of goods

መለኪያ

 

ብዛት

 

ምርመራ

 

1

ሎት-1

Drilling, Construction and Pumping Test of 500+20% Meter 1 (one) Deep Production Water Well

በቁጥር

1

 

2

ሎት_2

Drilling, Construction and Pumping Test of 350+20% Meter 1 (one) Deep Production Water Well

በቁጥር

1

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል።

1. የዘመኑን ግብር ከፍለዉ በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN/ የቫት ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የንግድ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸዉ መሆን አለበት። ተጫራቾች እነዚህንና ሌሎች ተያያዥነት ያላቸዉን መረጃዎች ኮፒ በማድረግ በጀርባዉ ፊርማና ማህተም በማድረግ በመጫረቻ ሰነዶቻቸው ላይ ማካተት ይጠበቅባቸዋል።

2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የሚሆን ለ60 ቀን እና ከዚያ በላይ ጸንቶ የሚቆይ ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ ለሎት-1 ብር 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር/፣ለሎት_2 350,000.00 /ሶስት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር/ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲ.ፒ. ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በማሰራት ማስያዝ አለባቸዉ።

3. የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 20 ሃያ ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በመምጣት የማይመለስ ብር 1,000 አንድ ሺህ ብር በውሀ ስራዎች ኮርፖሬሽን ባህር ዳር ከተማ ከሚገኘው ከኮርፖሬሽኑ ዋና ግቢ ከጠቅላላ ሒሳብ ክፍል ቢሮ እና አዲስ አበባ ከሚገኘው ከአዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሳሪስ ቦንጋ ሆቴል ገባ ብሎ 100 ሜትር በመሄድ መግዛት ይችላሉ።

4. ተጫራቾች መወዳደሪያ ሀሳባቸዉን ማለትም የቴክኒክና የዋጋ ሰነዳቸዉን በሁለት ቅጅዎች ዋናና ቅጅ በማለት ቴክኒካልና ፋይናንሻል በተናጠል ለየብቻ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 20 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ ባህር ዳር ከተማ ከሚገኘው ዋናው መስሪያ ቤት ውሃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ከግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 25 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

5. የቴክኒካል ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ዳይሬክትሬት ቢሮ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ20ኛው በተገኙበት ከኮርፖሬሽኑ ዋናው መ/ቤት ግቢ ግዥና አቅርቦት ቀን በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት ይከፈታል ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ተዘግቶ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል።

6. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

7. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በኮርፖሬሽኑ ዋና መቤት ቢሮ ግዥ እና አቅርቦት ቢሮ 3ኛ ፎቅ ቁጥር 25 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም ስልክ ቀጥር 058 222 1479 መጠየቅ ይቻላሉ።

8. ማሳሰቢያ- አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የጨረታ ሰነድ መግዛት ብቻ እንጅ የጨረታ ፖስታ ማስገባት የሚቻለው ባህርዳር ዋናው መስሪያ ቤት መሆኑን እንገልፃለን።

አድራሻ: –

ውሀ ስራዎች ኮርፖሬሽን ዋናው መ/ቤት

ባህርዳር ከተማ ቀበሌ 14 የድሮው አዲናስ ጠቅላላ ሆስፒታል ፊት ለፊ ፖ.ሣ.ቁ 106

ስልክ ቁጥር 058 222 1479

ፋክስ

ባህር ዳር

የውኃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *