ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ. ለሰጠው የብድር ማካካሻነት የተረከባቸውን ንብረቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ. ለሰጠው የብድር ማካካሻነት የተረከባቸውን ንብረቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል


Reporter (Nov 01, 2026)

የቤቶች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡ 04/2026/27

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ. ለሰጠው የብድር ማካካሻነት በአዋጅ ቁጥር 97/1990 መሠረት የተረከባቸውን ከዚህ በታች በሠንጠረዥ የተመለከቱትን ንብረቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ተቁ

የንብረቱ ዓይነትና የሚሰጠው አገልግሎት

ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ

የቦታው ስፋት በካ.ሜትር

የካርታ ቁጥር

አበዳሪው ቅርንጫፍ

የጨረታ መነሻ ዋጋ

ከተማ

ክ/ከተማ

ቀበሌ/ ወረዳ

1

የታሸገ ውሃ ማቀነባበሪያ እና መጋዘን

ሸገር

ሰበታ

አዋስ

6000

WLBEN/7679

ሆሳዕና

28,000,000.00

2

መኖሪያ ቤት

ጎንደር

ሳንጃ

01

340

00 831

ጎንደር

1,400,000.00

3

መኖሪያ ቤት B+G+4 ህንጻ

አዲስ አበባ

ቂርቆስ

ወረዳ 01

133.35ካሜ × 4

114.01ካሜ × 1

000040101642 AA 000040101642 AA 000040101642 AA 000040101642 AA 000040101642 AA

ስታዲየም

65,000,000.00

4

መጋዘን

ሸገር

ገላን

ገላን ቀበሌ

6300

BMG/K/L/ I/TA/2014

ወሎሰፈር

95,000,000.00

5

የንግድ ሕንጻ (G+4)

ሻሸመኔ

ቡልቸና

05

889

163

አዳማ

60,000,000.00

የጨረታው ደንቦች፡–

1. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በባንኩ ስታዲየም ቅ/ፍ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል እና ግሎባል ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት ግዥና ፋሲሊቲ አስተዳደር መምሪያ /ናሽናል ቢዝነስ ሴንተር ሕንጻ ላይ 7ኛ ፎቅ/ በአካል በመቅረብ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ /ፎርም/ መውሰድ ይኖርባቸዋል።

2. ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋውን 20% (ሃያ በመቶ) በገንዘብ ክፍያ ማዘዣ /CPO/ በግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ. ስም በማሰራት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች ንብረቶቹን የሚገዙበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ በባንኩ ዋናው መ/ቤት ግዥና ፋሲሊቲ አስተዳደር መምሪያ /ናሽናል ቢዝነስ ሴንተር ሕንጻ 7ኛ ፎቅ/ በአካል በመቅረብ እስከ ሕዳር 9 ቀን 2019 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

4. ማንኛውም ተጫራች ሌሎች ተጫራቾች በሰጡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችልም።

5. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ያካተተ መሆን አለበት። ይህንንም በግልጽ ማሳየት ይኖርባቸዋል።

6. ተጫራች ድርጅት ከሆነ የታደሠ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት፣ ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርበታል።

7. አሸናፊ የሚሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ገንዘብ ሙሉ በሙሉ በ30 /ሠላሳ / ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ከባንኩ ጋር የሽያጭ ውል መግባት አለበት። ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብም ካሸነፈበት ገንዘብ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ማሸነፉ ከተገለጸለት በኋላ እስከ 30ኛው ቀን ድረስ አስፈላጊውን የሽያጭ ውል የማይፈጽም ከሆነ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል።

8. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት የጨረታ ዋጋ ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 /ስልሳ/ ቀናት ይሆናል።

9. በጨረታው የተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት የገንዘብ ክፍያ ማዘዣ (CPO) የጨረታው ሂደት ተጠናቆ ውሳኔ እንዳገኘ ተመላሽ ይደረጋል።

10. ንብረቱ በገዥው ስም እንዲዛወር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል የትብብር ደብዳቤ ይጽፋል።

11. ለመንግስት ማንኛውም ግብር፣ የሊዝ ክፍያ፣ ንብረት በማስተላለፍ ሂደት የሚኖር ክፍያ እና ሌሎች ማንኛውንም ክፍያዎች ገዢው ይከፍላል።

12. ጨረታው ሕዳር 9 ቀን 2019 ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዛው እለት ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ላይ በግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ. ዋናው መ/ቤት 7ኛ ወለል ላይ በሚገኘው የስብሰባ አደራሽ ይከፈታል።

13. መረጃ እና የንብረቶቹን አጠቃላይ ሁኔታ ማየት የሚፈልግ ተጫራች ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ. ዋናው መ/ቤት ግዥና ፋሲሊቲ አስተዳደር መምሪያ በስልክ ቁጥር 011 558 1204 ወይም 011 531 8097 በመደወል እና ቀጠሮ በማስያዝ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋት 2፡00 – 6፡00 ከሰዓት በኋላ ከ7፡00 — 11፡00 ሰዓት ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00 – 6፡00 ሰዓት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሕዳር 8 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ መጎብኘት ይችላል።

14. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በማንኛውም ጊዜ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለጋራ ስኬታችን!


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *