በልደታ ክፍለ ከተማ የደጃ/ባልቻ አባነፍሶ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በልደታ ክፍለ ከተማ የደጃ/ባልቻ አባነፍሶ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 02, 2026)

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር 001/2019

በልደታ ክፍለ ከተማ የደጃ/ባልቻ አባነፍሶ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት የሚያስፈልጋቸውን ዕቃዎች በሎቱ መሰረት፡–

  • ሎት 1 የደንብ ልብስ የጨረታ ማስከበሪያ ብር መጠን 13,000
  • ሎት 2 አላቂ የማስተማሪያ እና የፅህፈት መሳሪያዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር መጠን 11,000
  • ሎት 3 አላቂ የፅዳት እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር መጠን 8,000
  • ሎት 4 የጥገና እቃዎች እና የስራ እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር መጠን 5,000
  • ሎት 5 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችና (ኮምፒውተር እቃዎች) የጨረታ ማስከበሪያ ብር መጠን 30,000
  • ሎት 6 ፎቶ ኮፒ ማሽን ጥገና የጨረታ ማስከበሪያ ብር መጠን 4,000
  • ሎት 7 ቋሚ እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር መጠን 18,000
  • ሎት 8 የተለያዩ ህትመት የስራዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር መጠን 3,000
  • ሎት 9 የደንብ ልብስ ስፌት የጨረታ ማስከበሪያ ብር መጠን 3,000

ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩትን ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል

በዚህም መሰረት ፡–

1. በጨርታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን፤ ታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው በመንግስት ግ/ን/አስተዳደር ኤጀንሲ ደህረ ገፅ ላይ በአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡ የቲንና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተርጋገጠ ሲፒዩ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡

3. ተጫራቾች የጨርታውን ሰነድ በማይመለስ 200 ብር በመክፈል ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከ ት/ቤቱ ፋይናንስና ግዥ ንብረት አስተዳደር ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡

4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት በት/ቤቱ ፋይናንስ ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ለጨርታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

5. ተጫራቾች የሚወደደሩባቸውን እቃዎች ለእያንዳዳቸው ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ10 ኛው ቀን 11፡30 ታሸጎ በማግስቱ ከጠዋቱ 4፡30 ፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ይከፈታል፡፡ የመክፈቻው ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሰራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡

7. ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወደደሩባቸው ሎት 1፤ሎት 2፤ሎት 3፤ ሎት 4 ሎት 6፤ሎት 8 ፤ሎት 9 ላይ ናሙና ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ለሎት 5 እና ለሎት 7 በቀረቡ የፍላጎት መግለጫ መሰረት የተሟላ የፍላጎት መግለጫ ማዘጋጀትና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

8. የዘገየ ጨረታ እና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም ፡፡

9. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥው ፈፃሚ መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

10. ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ እና ጥያቄ፤ በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ዳርማር ጫማ ፋብሪካ አጠገብ ወይም ከልደታ ፍርድ ቤት ጀርባ ደጃ/ባልቻ አባነፍሶ 2ኛ ደረጃ ት/ ቤት 0118 685 799 ወይም 0118 964 301 ደዉሎ መጠየቅ ይቻላል።

በልደታ ክፍለ ከተማ የደጃ/ባልቻ አባነፍሶ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት