Addis Zemen (Nov 03, 2026)
1ኛ ዙር የጨረታ ማስታወቂያ
በልደታ ክ/ከ/ ስር የሚገኘው የዕውቀት ለህብረት 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በጨረታ ቁጥር 001/2019 መሰረት
- ሎት 1 የደንብ ልብስ
- ሎት 2 አላቂ የቢሮ እቃዎች
- ሎት 3 የህትመት ስራዎች
- ሎት 4 የትምህርት መሳሪያዎች
- ሎት 5 የፅዳት አላቂ ዕቃዎች
- ሎት 6 ልዩ ልዩ እቃዎች
- ሎት 7 የጥገና እቃዎች
- ሎት 8 ቐሚ የቢሮ እቃዎች
- ሎት 9 ቋሚ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
በዚህም መሠረት መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ሕጋዊ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
1. ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው የሀገር ውስጥ የዘመኑን ግብር አጠናቆ የከፈለ፡፡ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
2. በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡ በሚያቀርቡት የእቃ ዋጋ ከነቫቱ መጠቀስ አለበት፡፡
3. የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00-10፡00 ሠዓት በፋ/ግ/ን/አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 14 የጨረታ ሰነድ መግዛት ይቻላል፡፡
4. የጨረታ ማስከበሪያ ከሚጫረቱበት በእያንዳንዱ ሎት 2% (ሁለት ፐርሰንት) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ አለባቸው፡፡
5. ተወዳዳሪው አሸናፊ የሆነ ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ የግዢውን ግምታዊ ዋጋ 10% በቅድሚያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
6. ተጫራቾች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ናሙናው ጨረታው ከመከፈቱ ከሁለት ቀናት በፊት ማቅረብ ግዴታ ይኖርባቸዋል፤ ካላቀረቡ ግን ከጨረታው ይሰረዛሉ ፡፡
7. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከቀኑ ከጠዋቱ 3:00 ሰአት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በፋይናንስ ክፍል ይከፈታል፡፡
8. በጨረታው የሚቀርቡት ዕቃዎች የጥራት ደረጃውን የጠበቁ መሆን አለባቸው፡፡
9. ማንኛውም ተጫራች በግዥ ጨረታው ላይ ከተጠየቀው ውጪ ናሙና ማቅረብም ሆነ ናሙናው ላይ ምልክት ማድረግ ከውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡
ማሳሰቢያ፡– መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡– በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 ከኢትዮጵያ መድሃኒት ፋብሪካ ጀርባ ገባ ብሎ
ለበለጠ መረጃ፡– 0911-79-47-46 ወይም 0911 47 75-46
በልደታ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት