በሰሜን ጎንደር ዞን የዳባት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን በዳባት ወረዳ ለሁሉም ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ አላቂ የቢሮ ዕቃ (ሎት 1)፣ ኤሌክትሮኒክስ (ሎት 2) እና የመኪና መለዋወጫ ዕቃ (ሎት 3) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በሰሜን ጎንደር ዞን የዳባት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን በዳባት ወረዳ ለሁሉም ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ አላቂ የቢሮ ዕቃ (ሎት 1)፣ ኤሌክትሮኒክስ (ሎት 2) እና የመኪና መለዋወጫ ዕቃ (ሎት 3) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Be'kur (Nov 02, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በሰሜን ጎንደር ዞን የዳባት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን በዳባት ወረዳ ለሁሉም ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ

  • ሎት1. አላቂ የቢሮ ዕቃ፣
  • ሎት 2. ኤሌክትሮኒክስ እና
  • ሎት 3. የመኪና መለዋወጫ ዕቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

 ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1.  የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) የተቀበሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እና በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ አግባብ ያለው ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈለበት የግብር ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የሚጫረቱትን የግዥ መጠን ከብር 500,000 (አምስት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4.  ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የምትሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 100,000 (አንድ መቶ ሽህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም ከመስሪያ ቤቱ መሂ 1 በማስያዝ ጨረታው እስከ ሚከፈትበት ሰዓት ድረስ ዳባት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 23 ከረዳት ገንዘብ ያዥ በመቁረጥ ከኦርጅናል ፖስታ ውስጥ ከጨረታ ሰነድ ጋር በፖስታ በማሸግ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ይሁን እንጂ የጨረታ ማስከበሪያ ጥሬ ገንዘብ ፖስታ ውስጥ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አይፈቀድም፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀር ወይም የሚያስዙት ዋስትና ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተጫራቹ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር በማያያዝ ፖስታ ውስጥ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ዳባት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 23 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች ሰነዱን ሲሞሉ ሥርዝ ድልዝ የተሞላበት ሳይኖረው ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 23 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡
  8.  ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከጥቅምት 23/2019 እስከ ህዳር 2/2019 ዓ/ም ለ10 ተከታታይ ቀናት ይሆናል፡፡
  9. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 23 ህዳር 03/2019 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ ከረፋዱ 4፡30 ይከፈታል፡፡
  10. አሸናፊዉ ተጫራች አሸናፊ የሆነበትን ዕቃዎች ዳባት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ የመኪና መለዋወጫዉን ዕቃ ግን በጎንደር ከተማ ጋራዥ ማድረስ ይኖርበታል፡፡
  11. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የማወዳደሪያ ሀሳብ የጨረታው መዝጊያ ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የማወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
  12.  የጨረታዉ መዝጊያ ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የማወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለዉጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና እራሳቸዉን ማግለል አይችሉም፡፡
  13. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡ ሆኖም ጨረታዉ በመሰረዙ ተጫራቾች ለመወዳደር ላወጡት ወጭ መስሪያ ቤቱ ሀላፊነት የማይወስድ ይሆናል፡፡
  14.  የጨረታ መክፈቻ ቀኑ በዓል ወይም እሁድ እና ቅዳሜ ከሆነ በሚቀጥለዉ ሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
  15. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ቢያስፈልጋቸው በስራ ሂደቱ ቢሮ ቁጥር 23 ዘወትር በሥራ ሰዓት በአካል ቀርበው ወይም በስልክ ቁጥር 058 113 04 10/058 130 20 56 ደውለው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የዳባት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *