Be'kur (Nov 02, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በሰሜን ጎጃም አስተዳደር ዞን የደቡብ አቸፈር ወረዳ ገን/ኢኮ/ትብብር ጽ/ ቤት በወረዳው ላሉ ሴ/መ/ቤቶች ዓመታዊ ግዥ ማለትም፡-
- ሉት 1. አላቂ የጽህፈት መሳሪያ፣
- ሎት 2. ቋሚ የጽህፈት መሳሪያ፣
- ሎት 3. የጽዳት ዕቃ፣
- ሎት 4. የኤሌክትሮኒክስ ጥገና እንዲሁም
- ሎት 5. የኮምፒውተርና የፎቶ ኮፒ ቀለም ዋጋ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም መወዳደር የሚፈልጉ ማንኛውም ተጫራች ከዚህ በታች የተዘዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ እና በዘርፉ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ከብር 500,000 (አምስት መቶ ሽህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (የቫት) ተመዝጋቢ
መሆናቸውን የሚረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡ - ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና ሌሎች ማስረጃዎችን ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሠነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ደቡብ አቸፈር ወረዳ ገን/ኢኮ/ትብብር ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 04 ዘወትር በስራ ሰዓት ለእያንዳንዱ ሎት ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታውን ዝርዝር መረጃ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በየምድቡ በተለያየ ፖስታ በማድረግ በጥንቃቄ በማሸግ ደቡብ አቸፈር ወረዳ ገን/ኢኮ/ ትብብር ጽ/ቤት ግዥ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 4 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሠዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ የሚቆየው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀን ይቆይና በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡30 ታሽጎ ከረፋዱ 4፡40 ህጋዊ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ከ5 የቅሬታ ቀናት በኋላ በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መውሰድ አለበት፡፡ ውል የማይወስድ ከሆነ ግን ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስትውርስ ይሆናል፡፡
- የጨረታ ዉድድሩ የሚካሄደው በየሎቱ ጥቅል ድምር ስለሆነ ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሎት ሁሉንም መሙላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም (ሲፒኦ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈባቸውን እቃዎች የማውረጃ እና የማስጫኛ እንዲሁም የትራንስፖርት ወጪውን ችሎ ደቡብ አቸፈር ወረዳ ገን/ኢኮ/ልማት ጽ/ቤት በየንብረት ክፍሉ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ በስልክ ቁጥር 09 18 80 32 45 በመደወል ወይም ቢሮ ቁጥር 4 በአካል በመምጣት መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
የደቡብ አቸፈር ወረዳ ገን/ኢኮ/
ትብብር/ጽ/ቤት