በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሰሜን ሸዋ ዞን ለባሶና ወራና ወረዳ ፍርድ ቤት እና ለቀይት ንዑስ ወረዳ ፍ/ቤት አገልግሎት የሚውል እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሰሜን ሸዋ ዞን ለባሶና ወራና ወረዳ ፍርድ ቤት እና ለቀይት ንዑስ ወረዳ ፍ/ቤት አገልግሎት የሚውል እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 02, 2026)

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ብሄራዊ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሰሜን ሸዋ ዞን ለባሶና ወራና ወረዳ ፍርድ ቤት እና ለቀይት ንዑስ ወረዳ ፍ/ቤት አገልግሎት የሚውል፡-

  1. ደንብ ልብስ ብትን ጨርቅ ፤ የተዘጋጁ ልብሶች ፤ የቆዳ ጫማዎች አና የፕላስቲክ ጫማዎች
  2.  አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች
  3. ልዩልዩ ህትመቶች
  4.  የጽዳት እቃዎች
  5. አላቂ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
  6. የሚሰሩ እና የተዘጋጁ የቢሮ ቋሚ እቃዎች
  7. ለቢሮ እድሳት የሚያገለግሉ እቃዎች
  8. ልዩ ልዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጥገና እና
  9.  ለችሎት የሚያገለግሉ መጽሀፍቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡-

  1.  በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ነምበር ያላቸው
  3. ተጫራቾች የሚጠበቅባቸውን ግብር የከፈሉ ስለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው
  4. የግዥው መጠን ከብር 500,000 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
  5. የጨረታ ውድድሩ በጥቅል ዋጋ ላይ የተመሰረተ ነው
  6. በነጠላ ዋጋው እና በጠቅላላ ዋጋው ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ከጨረታ ውጭ ይደረጋል ተጫራቾች በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ከቀን 23/2/2019 ዓ.ም ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ከባሶና ወራና ወረዳ ፍ/ቤት ደ/ብረሃን ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 የአገልግሎቱን ዓይነት ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ::

ተጫራቾች በተራ ቁጥር ከ 1 እስከ 9 የተጠቀሰውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 / ሁለት መቶ ብር/ ብቻ ለእያንዳንዳቸው በመክፈል ከባሶና ወራና ፍ/ቤት ደ/ብርሃን ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 መግዛት ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች የሚወዳደሩበት የሚያቀርቡበትን የአገልግሎት ጠቅላላ ዋጋውን /ቫት/ ጨምሮ 1% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ ሲፒኦ / በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአንድ ፖስታ በጥንቃቄ ታሽጐ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ቀናት በባሶና ወራና ወረዳ ፍ/ቤት ደ/ብረሃን ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 11 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡30 ሰዓት ቀርበው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

ጨረታው በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 የጨረታ ሣጥኑ ታሽጐ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመ/ቤቱ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቁጥር 11 በይፋ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 11ኛው ቀን የስራ ቀን ላይ ካልዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ጨረታው የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ናሙና እንዲቀርብ የተጠየቁትን እቃዎች ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው:: ለበለጠ መረጃ መ/ቤቱ ድረስ በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0116376493 በመደወል መረዳት ይችላሉ

አሸናፊ ተጫራቾች እቃውን ለባሶና ወራና ወረዳ ፍ/ቤት ናሙና የተጠየቀውን በናሙናው መሰረት ናሙና የሌለውን በውሉ መሰረት በማቅረብ ገቢ ያደርጋል::

በሰሜን ሸዋ ዞን የባሶናወራና ወረዳ ፍ/ቤት

/ደብረ ብርሃን/