በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ለደቡብ ወሎ ብዝሀ ህይወት ጥበቃና ደን ልማት ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውሉ የችግኝ ማፍያ ፕላስቲክና ማጓጓዣ ካሳ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ለደቡብ ወሎ ብዝሀ ህይወት ጥበቃና ደን ልማት ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውሉ የችግኝ ማፍያ ፕላስቲክና ማጓጓዣ ካሳ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Be'kur (Nov 02, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር አብክመ /አካጥባ kfw/ግ/ጨ 01/2019

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ለደቡብ ወሎ ብዝሀ ህይወት ጥበቃና ደን ልማት ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውሉ

  •  የችግኝ ማፍያ ፕላስቲክና ማጓጓዣ ካሳ በፕሮጀክቱ በጀት በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚታሟሉ ህጋዊ ድርጅቶች በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል፡፡

  1.  በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. የግዥው መጠን ብር 500,000 (አምስት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ
    የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5.  የጨረታ መተማመኛ ቅፅ (ክፍል 4) ሞልተው ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  6.  የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማረጋገጫ የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  7.  ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1-6 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ የጨረታ ማስከበሪያቸውን እና የፋይናንሻል ሰነዳቸውን በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  8.  ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈልና ገንዘብ ያዥ ላይ ገቢ በማድረግ የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ፡፡
  9.  ተጫራቾች ግዥ የሚፈፀምላቸውን እቃዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች ለተወዳደሩበት ሎት ብር 70,000 (ሰባ ሽህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡ የልዩ አስተያየት ተጠቃሚ የሆኑ ድርጅቶች የሚያቀርቡት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ካደራጃቸው ተቋም የተሰጠ (በሃላፊ የተፈረመ) የድጋፍ ደብዳቤ ይሆናል፡፡ ከተጫራቾች የሚቀርቡት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጨረታው ዋጋ ፀንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን ቢያንስ ለተጨማሪ 28 ቀናት ፀንቶ መቆየት ይኖርበታል፡፡
  10. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ከጥቅምት 23/2019 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ህዳር 2/2019 ዓ.ም ለ10 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ይሆናል፡፡
  11.  ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ባሕር ዳር በሚገኘው የአብክመ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  12. ጨረታው ህዳር 3/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ተዘግቶ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ ውስጥ በይፋ ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  13.  አሸናፊው የሚለየው በጥቅል (በሎት) ዋጋ ይሆናል፡፡
  14. ተጫራቾች ዋጋ የሞሉበት እያንዳንዱ ቅፅ ላይ የድርጅቱን ማህተም ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ አለማድረግ ከጨረታ ውድድር ውጪ ያስፈልጋል፡፡
  15.  በአንድ ሎት ላይ በከፊል ዋጋ ሞልቶ መወዳደር ከዋጋ ውድድር ውጪ ያስፈርልጋል፡፡
  16. በዋጋ መሙያ በእያንዳንዱ ገፅ ላይ የድርጅቱን ማህተም ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ አለማድረግ ከውድድር ውጪ ያስፈልጋል፡፡
  17.  የርክክብ ቦታው በደቡብ ወሎ ዞን አካባቢ ጥበቃ ተ/ጽ/ቤት ደሴ እቃ ግምጃ ቤት ውስጥ ይሆናል፡፡
  18.  መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  19. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ወይም ማብራሪያ መጠየቅ ቢፈልጉ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 5ኛው ቀን ድረስ ብቻ በስልክ ቁጥር 058 320 6206 በመደወል ወይም በአካል በመምጣት ማግኘት ይችላሉ፡፡

ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የእቃ ናሙና የጨረታ ሰነዱን ሲወስዱ መመልከት ይኖርባቸዋል

የአብክመ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን

ባሕር ዳር


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *