Addis Zemen (Nov 02, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኩታበር ወረዳ ፍ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በጋዜጣ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን
- ሎት 1 አላቂ የጽሕፈት መሳሪያዎች
- ሎት 2 ቋሚ እቃ
- ሎት 3 የቢሮ ማሽነሪ፣
- ሎት4 ህትመት፣
- ሎት 5 የደንብ ልብስ፣
- ሎት 6 አላቂ የፅዳት እቃዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፡፡
4 የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ/ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
6 የሚገዙ እቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (specfication) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል በኩታበር ወረዳ ፍ/ ቤት ግዥ/ን/አስ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 10 ከ27/2/019 ዓ.ም ጀምሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲ.ፒ.ኦ. ለሚወዳደሩበት ብር ወይም ለሚሰራው ስራ ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም ከታመነበት በባንክ በቼክ ማስያዝ አለባቸው::
9.ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡንም ኦርጂናልና ኮፒ በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በኩታበር ወረዳ ፍ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 10 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ቀን ከ27/2/2019 ዓም ጀምሮ እስከ 18/3/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡
10, ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 10 በቀን 18/3/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ይከፈታል ተጫራቾች ለእቃው ዓይነትም ሆነ መጠን በጨረታው በሙሉ ወይም በከፊል መሳተፍ ይችላሉ፡፡ሆኖም አንድ ተጫራች በአንድ ሎት ውስጥ ከተዘረዘሩት የእቃ ዓይነቶች መካከል ከፋፍሎ መጫረት አይችልም፡፡
11. መ/ቤቱ ጨረታውን በድምር ወይም በነጠላ ዋጋ የማወዳደር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ጨረታው በመሰረዙ ምክንያት ተጫራቾች ላወጡት ወጭ መ/ቤቱ ሃላፊነት አይወስድም፡፡
12- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈለጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥ 09 14 068 901 ወይም 09 20 79 43 36 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት
የኩታበር ወረዳ ፍ/ቤት