Addis Zemen (Nov 02, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዢ መለያ ቁጥር 01/2018
በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ በወረዳ 9 ስር የሚገኘው ቂሊንጦ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን በየሎቱ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች በማየት መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ሎት 1. 6211/ደንብ ልብስ 30,00000
- ሎት 2. 6212/ አላቂ የቢሮ ዕቃ 20,000
- ሎት 3. 6213/ የህትመት ውጤቶች 10,000.00
- ሎት4. 6214/ የትምህርት ዕቃዎች 10,000.00
- ሎት 5. 6215 የትምህርት ዕቃዎች 25,000.00
- ሎት 6. 6218/ አላቂ የፅዳት ዕቃዎች 30,000.00
- ሎት 7. 6219/ ልዩ ልዩ ዕቃዎች 30,000.00
- ሎት 8. 6313/ ቋሚ ዕቃዎች 60,000.00
1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ እና ቲን ነምበር /TIN NO/ ያላቸው::
2. የዘመኑን ግብር የከፈሉና በአቅራቢዎች ስም ዝርዝር ላይ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገጽ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
3. በተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
4. የጨረታ ማስከበሪያ የሚወዳደሩበት ሎት ከላይ በየሎቱ ጎን የተጠቀሰውን የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ /ሲፒኦ/ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት።
5. የጨረታ ሰነዱ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ የማይመለስ 400/አራት መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በት/ቤቱ ፋይናንስ በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነዱን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል ::
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒውን በመለየት በፖስታ በማሸግ ት/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
8. ጨረታው የሚዘጋው የሚታሸገው/ጨረታው በጋዜጣ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ11 ኛ ቀን (በስራ ቀናት) ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ይሆናል፡፡ ጨረታው የሚከፈተው በዚያው ቀን ማለትም ጨረታው በጋዜጣ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ11 ኛው ቀን (በስራ ቀናት) ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ይሆናል፡፡
9. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈውን ዕቃ በሚደረግ የውል ስምምነት መሰረት በራሱ ትራንስፖርት ቂሊንጦ 2ተኛ/ደ/ት/ቤት አስቱ ዩኒቨርሲቲ ፊት ለፊት በሚገኘው ትምህርት ቤታችን በመገኘት በንብረት ክፍል ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
10. ተጫራቾች በሚያቀርቧቸው ዕቃዎች ጨረታ ከመከፈቱ በፊት የጨረታ ሰነድ ስታስገቡ ከእያንዳንዱ አላቂና ቋሚ እቃዎችን በመለየት ናሙና /ሳምፕል/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪ መምጣት የማይችሉ ከባድና በባህሪያቸው የተለዩ እቃዎችን በፎቶ ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡
11. ተጫራቾች በምታቀርቡት ናሙና/ሳምፕል/ ላይ ምንም አይነት ማህተም ስልክ ቁጥር እና ሌሎች ምልክቶች እንዳይኖር ከወዲሁ እናሳስባለን፡፡ ምልክት ያለበት ሳምፕል እና የጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ፣ ፍሉድ ማስገባት ጨረታውን ውድቅ ያደርገዋል፡፡
12 ተጫራቾች ጨረታ በሚዘጋበትና በሚከፈትበት ሰአት ማለትም ጨረታው በጋዜጣ ከተገለጸበት በ11 ኛው ቀን (በስራ ቀናት) ከጠዋቱ 4:00 ሰአት ጀምሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው መገኘት ይኖርባቸዋል፡፡
13. የጨረታ አሸናፊ ሆነው ከተገኙ በኋላ 10% /አስር ፐርሰንት/ ባሸነፉበት ዕቃ መሰረት የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል::
14. መ/ቤቱ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ይሆናል፡፡
15. በበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር— 09-11-421 605 / 09-22-024 252/ ብለው ይደውሉ፡
16. በጥቃቀንና አነስተኛ ወይም ካደራጃቸው መስሪያ ቤት የድጋፍ ደብዳቤ ይዘው የሚጫረቱ ተጫራቾች ከሆኑ ምን አይነት ምርቶ እንደሚያመርቱ እና የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል የሀገር ውስጥ ምርት ችርቻሮ ወይም ጅምላ ንግድ ከሆነ ደግሞ ከአምራቹ የተሰጣቸውን ፈቃድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል ካልሆነ ግን እንደማንኛውም ተጫራች ሰነድ በመግዛትና የጨረታ ማስከበሪያ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ መወዳደር ይችላሉ፡፡
አድራሻ፤ አስቱ ዩኒቨርሲቲ ፊት ለፊት ወይም በመገንባት ላይ ያለው አዲሱ የአ/ቃ/ቃ/ክ/ከ ወረዳ ዘጠኝ ህንጻ ጀርባ ያለው ት/ቤት
በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ በወረዳ 9 የቂሊንጦ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት